የሃዘን እንጉርጉሮ በጭንቅላቱ ላይ የሃገሩን ባንደራ ጠምጥሞ መንገድ ላይ ለቀረው ወንድሜ
- የሃዘን እንጉርጉሮ በጭንቅላቱ ላይ የሃገሩን ባንደራ ጠምጥሞ መንገድ ላይ ለቀረው ወንድሜሃገሩን ወዶ በሃገሩ እንዳይኖር
ኑሮ ፖለቲካው ከሬት በላይ ቢመር
እናም
ወጥቶ ተሰደደ ወደማያውቀው አገር
ፓለቲካ ሸሽቶ፣ ኑሮን አሽንፎ ቤተሰቡን ሊጦርግን
ሳውዲ አሉት ስምሽን አልቃሽ ይጥራውና
እንስሳው ህዝብሽ ወንድሜን ገደለው እንዲያው በጎዳና
ውሻ ነው እያሉ ሰውን ‘ማያከብሩት
በዱላ ነረቱት በጥፊም አጮሉት
አሱም አቅም ቢያጣ መንገድ ላይ ወደቀ
ወገን እንደሌለው ሞቶ ተጎተተ!ኢትዮጵያዊ መሆኔን ኢትዮጵያዊ ቢያዬው ብሎ በማሰቡ
ጥሎ ቢሰደድም አገሩን ምድሩን ስለሚወድ ከልቡ
እየደበደቡት ብሎ ችላ ስቃዩን
ራሱ ላይ አስሮ የእናት ሰንደቁን
በዚያው አሸለበ ወደማይቀረው ጉዞ
ከባንደራዋ ጋር የሃገሩን ፍቅር በነፍሱ ውስጥ ይዞ
No comments:
Post a Comment