ከ 1400 አመት በፊት ለነቢዩ መሀመድ ተከታዮች የፖለቲካ ጥገኝነት በመስጠት በዘመኑ የነበሩ የኢትዮፕያ ገዚዎች በጎ ተግባር ሰርተዋል:: የቅርብ ጊዜውን የ50 አመት ታሪክ ስንመለከትም የሳውዲ ዜጎች የሚላስ የሚቀመስ ካልነበረባቸው የሳውዲ ምድረ በዳዎች ተሰደው በአገራችን በሰላም ሲኖሩና ሲነግዱ የነበረ ከመሆኑም በተጨማሪ በበርካታ የአገራችን ዋና ከተማዎች 'አረብ ሰፈር' የሚባሉ መንደሮችን በስማቸው እስከ ማሰየም ደርሰው ነበር:: ባለፉት አራት 10 አመታት የሚላስ የሚቀመስ ያልነበራት በረሃማዋ ሳውዲ አረቢያ ከፍተኛ የነዳጅ ክምችት በማግኘት በችጋር የተበተኑ ዜጉቹዋን ስትሰበስብ በተቃራኒው እኛ የሁዋሊዮሽ ቁልቁል በመውረድ ዜጎቻችንን በመላው አለም በስደት ለመበተን ተገደናል:: ሰሞኑን በሳውዲ አረቢያ በዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ግፍና መከራ በእጅጉ የሚያሳዝን ከመሆኑም በተጨማሪ ገዚዎቻችን ለአገሪቱ ሀብትና ለስልጣናቸው ካልሆነ በቀር ለአገሪቱ ዜጎች ደንታ ቢስ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ነው:: ፔትሮ ዶላር ያሰከረው የሳውዲ ንጉሳዊ አስተዳደርስ ህገ ወጥ ስደተኞችን ከአገሩ ከማሰወጣት ባለፈ ግድያ ድብደባና እንግልት ያውም በክፉ ቀን ደግ ባረጉለት ኢትዮፕያውያን ስደተኞች ላይ የሚፈጽመው በምን ምክንያት ነው? የኢትዮፕያ መንግስትስ ከሳውዲ የሚያገኘው ፍርፋሪ በዜጎቹ ላይ ከሚደርሰው አሰቃቂ መከራ በልጦበት ዝምታን የሚመርጠው እስከመቼ ነው?
'ስጋዬን ሳሸሽ ካገሬ አሞራ.

No comments:
Post a Comment