Monday, November 18, 2013

በየወህኒ ቤቱ እና በግዜያዊ መጠለያው የታጎሩትን በመቶሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያኖች ወደ ሃገራቸው ለመለስ በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ ኤንባሲ የተቀላጠፍ አሰራር እንደሌለው ተገለጸ ።

 
በየወህኒ ቤቱ እና በግዜያዊ መጠለያው የታጎሩትን በመቶሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያኖች ወደ ሃገራቸው ለመለስ በሚደረገው ጥረት በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ ኤንባሲ የተቀላጠፍ አሰራር እንደሌለው ተገለጸ ።
ዛሬ ከቀትር በሃላ ለሳውዲ ዋናው ቴሊቪዥን ጣቢያ በኢትዮጵያውኑ ስደተኞች አያያዝ ዙሪያ እና ተዛማጅ ጉዳዩች ከጋዜጠኛ ይቀርብላቸው ለነበረ ጥያቄ ማብራሪያ ሲሰጡ የነበሩ አንድ የሪያድ ፖሊስ አዝዥ አሁን ኢትዮጵያውያኑ ወደ ሃገር በመሸኘቱ ረገድ የተጀመረው እንቅስቃሴ ያለኢትዮጵያ ኤንባሲ የይለፍ ወረቀት ምንም ነገር ማድረግ እንደማይችሉ ገልጸው የማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሰነድ በኤንባሲው በኩል አልቆ ሲደርሳቸው ኢትዮጵያውያኑን ወደ ሃገራቸው እንዲገቡ ለማድረግ ፈጣን አሰራር እንደ ቀየሱ የሳውዲ ፖሊስ አዝዡ አክለው ገልጸዋል ።ከዚህ ጋር በማያያዝ የኢትዮጵያ ኤንባሲን ዘገምተኛ ሰራር ለመቃኘት የሞከረው የሳውዲ ጋዜጠኛ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ሰራተኛ ለሆኑ አንድ ግለሰብ በዚህ ዙሪያ ላቀረበላቸው ጥያቄ የሰዎችን ስም እና አድራሻ በነጭ ወረቀት አልይ በመመዝገብ ኤንባሲው የተቀላጠፈ አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆኑንን ገልጸዋል።
አሁን ዘግይቶ የድረሰ ዜና ማምሻውን በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት አዳራሽ፡እና በጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት ሰሞኑንን ሳውዲ አረቢያ ውስጥ፡በተፈጠረው ጉዳይ ከኢትዮጵያ ከመጡ የውጭ፡ጉዳይ ሚንስቴር ሎኡካን ቡድን ጋር ህዝቡ ውይይት እንደሚያደርግ ይጠበቃል።
Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ

No comments:

Post a Comment