ኖርወጂያዊ ተመራማሪ የአፍሪካን ስታስትስቲክስ የሚተቸው መጽሓፋቸው
ኖርወጂያዊው ተመራማሪ ሞርተን የርቨን የአፍሪቃን ዕድገት ታሪክ እንዳለ መቀበል የለብንም ሲሉ ያስጠንቅቃሉ፣ ፣ .
የአፍሪካ የኤኮኖሚ ሁኔታ የሚገልጽ አሃዝ ለ ጥናት፣ በሚሊዮን ለሚቆጠር እርዳታ መስጠት መሰረት ተደርጎ ይወሰዳል፣ ፣
- የብዙ አፍሪቃዊ ሃገሮች ስትትስቲክስ በ አጠራጣሪ ግምት ላይ የሚመሰረት ነው፣ ፣ ትልቅ የእዉቀት ችግር አለብን ይላሉ የርቨን፣ ፣
የርቨን በ ሲሞን ፍረዘር ዩኒቨርሲቲ መምህር ሲሆኑ በ ዓመቱ መጀመርያ ነበር "ፑር ናምበርስ" የተሰኘውን መጽሓፋቸው ያስመረቁት፣ ፣
Publisert: 02.10.2013 20:08
መጽሓፉ በአፍሪቃ ሃገራት የኑሮ እድገት ድረጃና በ ልማት ላይ የሚያተኩር ከመሆኑም በላይ የአገራቱ ሁኔታ ዋና አመላካች የሆነው "ግሮስ ናሽናል ፕሮዳክት" ጠቅላላ ሃገራዊ ምርት የሚሰላበት መንገደ ጎደሎዎች ያሉት መሆኑን የሚያጋልጥ ነው፣ ፣
አጠቃላይ የሃግራት ምርት የሚያሰሉ ዘዘንጠረዥ የሚያመነጩ ድርጅቶች ማዲሶን፣ የዓለም ባንክና ፐን ዎርልድ ናቸው፣ ፣
የርቨን የሃገራትን ሃብት በ ሶስቱ ሰንጠረዦች ሲሰሉ ልዩነት እንደሚያሳዩ በመጽሓፋቸው አመላክተዋል፣ ፣
ለምሳሌ ሞዛምቢክ በ ዓለም ባንክ ስሌት 37ኞች ከ 45 ሃገራት በመሆን በድህነት ስትፈረጅ በ ፐን ዎርልድ መለኪያ ደግሞ 23ኛ ከ 45 ሃገራት ወጥታለች፣ ፣ በሶስተኛው ማስያ ዘዴ በ ማዲሶን ደግሞ 11ኛ በመሆን ከ ሃብታሞቹ አንዷ ተደርጋ ትቆጠራለች፣ ፣ ጋና እሴትና ጸጋዋን የምትመጥንበት ዘዴ በ2010 ዓ.ም. ስትቀይር በአንድ ቀን ሕዝቦቿ 60 በመቶ ሃብታም ሆኑ፣ ፣ በወረቀት፣ ፣
መጽሃፋ አከራካሪ መሆኑ አልቀረም፣ ፣ የደቡብ አፍሪቃ የስታትስቲክስ ምሁራን የርቨንን እንዳልተቀበሏቸውና በይፋ መቃወማቸው ሲዘገብ በአንጻሩ መጽሓፉ በ ማይክሮሶፍት ባለቤትና መስራች ቢል ገትስ አድናቆት ተችሮታል፣ ፣
No comments:
Post a Comment