በደቡብ ክልል በጋሞጎፋ ዞን በጨንጫ ወረዳ የሚገኙ የተለያዩ ትምህርት ቤት መምህራን ለአባይ ግድብ ማሰሪያ በሚል ከደሞዛቸው ላይ ገንዘብ መቆረጡን ተከትሎ ካለፉት 3 ቀናት ጀምሮ የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን ኢሳት ጥቅምት 7 ቀን 2013 ዓ ም ባሰራጨው ዜና አመለከተ።
የጨንጫ ፣ ጭነቶ፣ ጦሎላ፣ ጨፌ፣ ጺዳ እና ቱክሻ ትምህርት ቤቶች መምህራን በአድማ ላይ መሆናቸውን ተከትሎ ትምህርት ቤቶች ተዘግተው ተማሪዎች ቤታቸው ለመቀመጥ ተገደዋል። የወረዳው እና የዞን መምህራን ማህበር ከመምህራኑ ጋር በመሆን አድማውን እያስተባበሩ ሲሆን፣ አድማው ወደ ሌሎች ትምህርት ቤቶች እና አካባቢዎች ሊዛመት እንደሚችል መምህራኑ ተናግረዋል።

መምህራን “ደሞዛችን በግድ መቆረጡ አንሶ፣ እኛ በጠየቅነው ቀርቶ ባልጠየቅነው ወር ለምን ይቆረጥብናል ” በማለት አድማውን እንደ ጀመሩ አንድ መምህር እንደገለጹለት ያመለከተው ኢሳት መምህራን የአንድ አመት ደሞዛቸውን ከተቆረጠ በሁዋላ፣ ከመስከረም ጀምሮ ደግሞ ሁለተኛውን ዙር ማስቆረጥ ጀምረዋል ያለው ኢሳት የኢትዮጵያ መንግስት መምህራን ለአባይ ግድብ ማሰሪያ በፈቃዳቸው ከደሞዛቸው እንዳስቆረጡ በተደጋጋሚ ሲገልጽ መቆየቱንም አስታውሷል።
source: golgul.com
No comments:
Post a Comment