የኢሳት መንቀፍ የኢትዮጵያውያንን ተስፋ ያጨልማል!!!
በኢትዮጵያ ውስጥ የሚዲያ እድገት እንዳይኖር እና እድገቱን በጊዜ ለማቀጨጭ ይቻለው ዘንድ ጋዜጠኞችን በተለያዩ ምክንያቶች በማንገላታት ከስራቸው ውጭ በማድረግ ላይ የሚገኘው የወያኔው መንግስት ዘንድሮም ጋዜጠኞችን በአሸባሪነት ክስ እያቀረበ እንደሚገኙ የሚታወስ ነው። በአለም አቀፍ ዘንድ አሸባሪ የሚለውን ቃል የሚጠቀሙበት ከጦር መሳሪያ ጋር በተያያዘ መልኩ አጥፍቶ መጥፋት ሲያደርጉ ወይንም ሌሎችን ለጉዳት ሲጥሉ ሲሆን ይህም በከፍተኛ ደረጃ ላይ መንግስትን ብቻ ሳይሆን ሃገርንም ህዝብንም ለጉዳት እንደሚዳርግ ስለሚታመን አሸባሪነትን ለመከላከል ልዩ ዝግጅት ያደራሉ በዚህ የአሸባሪነት ሁኔታ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈረጁት ግን እስክሪፕቶ ይዘው ያዩትን የሰሙትን ..በአቅራቢያው በመሄድ መረጃ በማሰባሰብ ለህዝብ ጆሮ እንዲደርስ የሚያደርጉትን የጋዜጠኝነት ሙያ ያላቸውን ሰዎች መሆኑ እጅግ አሳፋሪ እንደሆነ ተገልጾአል ባሳለፍናቸው አምስት አመታት ወስጥ ከ125 በላይ ጋዜጠኞች በተለያዩ አገራት የተሰደዱ ሲሆን በአሁን ሰአትም ብዙዎቹ አገራቸውን ጥለው በስደት አለም ላይ ከፍተኛ ችግር እና መከራን እየተላበሱ ይገኛሉ ይህም የሚሆነው የፍትህ እጦት በሌለባት አገር የመገናኛ ብዙሃን እንደማያገለገል በመንግስታቶች ስለታወጀ ሳይሆን አይቀርም ። የወያኔ መንግስት ለምንድን ነው ህዝብን በሰቆቃ ማኖር የሚፈልገው ? ለምንስ ጋዜጠኞችን ማሰር አስፈለገ ? ለምንስ የወያኔ መንግስት የቤተመንግስት በር እንደሌሎች የአፍሪካ አገሮች ለጋዜጠኞች ክፍት አላደረገም ?ለምን ለግል ሚዲያዎች ቦታ አይሰጥም ብለን እንኳን እራሳችንን ብንጠይቅ በውስጣቸው የሚሰራው ነገር እንደሚጋለጥባቸው ስለሚያውቁት ከማናቸውም ነገሮች ለመሸሽ የሚያስችላቸው ቀላሉ ዘዴ ጋዜጠኞችን ከጥቅም ውጭ ማድረግ አንዱ ሲሆን ሁለተናው የስራው ባለቤት የሆኑትን ከንግዱ ማህበረሰብ የህትመት እቃዎችን ጣራ በመስቀል ከንግዱ ማሰውጣት መሆኑ ይታወቃል
የኢሳት መንቀፍ የኢትዮጵያውያንን ተስፋ ያጨልማል፤ አንፈራጥጠው ከላይ ቤት እታች ቤት እየቀላወጡ
አካላቸውን፣ አእምሮአቸውንና መንፈሳቸውን የሚያባልጉ ሰዎችን ያበራክታል፤ የድብቅብቆሽ ዓለምን እየፈጠሩየጠራውን ከደፈረሰው፣ የጸዳውን ከአደፈው፣ ሳይለዩ ለሚያወሩት ደካሞች ሜዳውን ያሰፋላቸዋል፤ የወያኔ/ኢሕአዴግን ፍርሃት ወደመርበድበድ ይለውጠዋል፤ የጦርነት ጥሩምባ ለሚነፉትም ሜዳውን እያሳየ የቀረርቶ በርይከፍትላቸዋል፤ ይህ ሁሉ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሰላምንና ስምምነትን፣ እድገትንና ብልጽግናን፣ ኩራትንና ክብርንአያስገኝም።
የሚዲያ ባለሙያዎች የሚዲያ ነፃነት የሚረጋገጠው ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ሲረጋገጥ መሆኑን አምነው በቅድሚያ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዳይገነባ አንቀው በመያዝ የህዝቡንና የሚዲያውን ነፃነት ጨፍላቂ የሆኑትን አምባገነን ስርዓቶች መታገል እንደሚገባ፤ ለዚህም ሚዲያው አበክሮ እንዲሰራ ጥሪ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በአምባገነናዊ ስርዓት ውስጥም ነፃ ሚዲያ መመስረት የማይታሰብ መሆኑን ቢታወቅም አያሌ ባለሙያተኞች መሰዋትነት እየከፈሉ ይገኛሉ።
ወደ ሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ስንመጣም ስርዓቱ ለነፃ ሚዲያ ማበብ ቁርጠኝነት ያነሰው በመሆኑ ከማስመሰል ባለፈና ለስርዓቱ አጨብጫቢ የሆኑ ሚዲያዎችን ከመቀፍቀፍ በዘለለ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓቱ መጎልበት አስተዋፅኦ የሚያደርጉ ተች ሚዲያዎችን ሊፈጥር አልቻለም፡፡ ይልቁንም በተቃራኒው በግል ተነሳሽነት ለመንቀሳቀስ የሚሞክሩትን ከማጥፋትና ጋዜጠኞችን ከማሰር ቦዝኖ አያውቅም፡፡ በተለይም ነፃው ፕሬስ በመንግስት የተቀነባበረና ከፍተኛ ጥቃት ሰለባ ነው፡፡ ስለዚህ በሀገራችን የተገኙ የሚዲያ ባለቤቶች የኢትዮጵያ መንግስት ለሚዲያ ነፃነት መረጋገጥ እንዲሰራ ተጨባጩን የሀገራችንን የሚዲያ እድገት እንዲመረምሩ ጥሪ ማስተላለፍ ያስፈልጋል፡፡
ፍትሕና መልካም አስተዳደር ለኅብረተሰቡም ሆነ ለግለሰብ የሚፈጥረው ደስታና እርካታ ከተራ የመልበስ፣ የመጉረስ፣ የመጎንጨት ደስታና እርካታ በእጅጉ የተለየ ነው፡፡ ሰው በሰው ልጅነቱ፣ ሰው በዜግነቱ እንዲኮራ የሚያደርግና ይበልጥ አገሩንና ወገኑን እንዲያገለግል የሚያስችለው እርካታ ነው፡፡ ጊዜያዊ እርካታ ሳይሆን ዘላቂ፡፡በዚህም ምክንያት ነው ደግመን ደጋግመን ልዩ ትኩረት ለመልካም አስተዳደርና ለፍትሕ ይሰጥ የምንለው፡፡ ደግመን ደጋግመን ፍትሕንና መልካም አስተዳደርን እውን የሚያደርጉ የሕገ መንግሥት ድንጋጌዎች ተግባር ላይ ይዋሉ የምንለው፡፡ ለዚህም ነው ደግመን ደጋግመን የሕዝብን መልካም አስተዳደርና ፍትሕ የሚረግጡ፣ የሚሸጡ፣ የሚለውጡ ተጠያቂ ይሁኑ፣ ለፍርድ ይቅረቡ የምንለው፡፡
የውኃ ጥም የሚረካው ውኃ ፍሪጅ ውስጥ ስለተቀመጠ አይደለም፡፡ ሱቅ ውስጥም ስለተደረደረ አይደለም፡፡ ምንጮች ውኃ ስላላቸው አይደለም፡፡ የውኃ ማስታወቂያዎች ስለተሰሙ፣ ስለተነበቡና ስለታዩ አይደለም፡፡ በተጨባጭ የተጠማው ሰው ማግኘትና መጠጣት ሲችል ነው፡፡
በመጨረሻም በኢትዮጵያችን ያለው አምባገነን ስርዓት በርካታ ጋዜጠኞችን እስር ቤት አጉሯል፡፡ ጠንካራ የግል ጋዜጦችንም ዘግቷል፡፡ ለክቡራን ሚዲያ ባለቤቶችና አዘጋጅ ለሆነው አካል ጥያቄ አቀባለው ስለ እኛኑ ማለቴ ነው፡፡ በሀገራችን ሃሳባቸውን በነፃነት ስለገለፁ ብቻ ለእስር የተዳረጉት አንዲፈቱና የሚዲያ ባለሙዎችም ይህንን በአካል ቃሊቲ በመሄድ ከእስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት ዓለሙ፣ የሱፍ ጌታቸውና ዝዋይ የሚገኘውን ውብሸት ታየን በማነጋገር እንዲያረጋግጡ ጥሪ መገፋፋት ያስፈልጋል፡፡ እግረ መንገዳችሁንም በወያኔ ስርዓት ውስጥ ነፃ ፕሬስ ምን ማለት እንደሆነ ትረዳላችሁ፤ ስንቶቹ ሀገራቸውን ጥለው እንደተሰደዱ ታውቃላችሁ።
በአጠቃላይ ሲታይ ፍትሕና መልካም አስተዳደር በመጓደሉ የሕዝብም የዜጋም ልብ እየቆሰለ ነው፡፡ ተስፋው እየጨለመ ነው፡፡ እኔ ኢትዮጵያዊ አይደለሁምን እያሰኘ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ለእኔ ምኔ ናት እያስባለ ነው፡፡
በተግባር በአስቸኳይ እንለውጠው፡፡ ጠንካራ፣ ፈጣን፣ ቆራጥ የሕዝብ የጋራ ዕርምጃ ይኑር፡፡ መልካም አስተዳደር እውን ይሁን፡፡ ሕዝብ በአገሩ ይኩራ፤ በኢትዮጵያዊነቱ ይመካ፡፡ በአገሩ ኮርቶ አገሩን ያክብር፡፡
ፍትሕ ይንገሥ፡፡
ክብርና ነፃነት ለነፃ ሚዲያና ጋዜጠኞች!!!
No comments:
Post a Comment