Wednesday, February 12, 2014

"አይ ስብሐት ነጋ!" በማለት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም የፃፉት አርቲክል እኚህን ጉምቱ የወያነ መንፈሳዊ አባት በአግባቡ ገልጿቸዋል ። ቃል ከቃል አዋደን፣አረፍተ ነገሮች ብናዳቅል ፕሮፌሰሩ አቦይ ስብሀትን ፍንትው አድርገው እንዳሳዩን የማመላከት ብቃት አይኖረውም። "....በኢትዮጵያ ስልጣን ሳይኖረው ባለሙሉ ስልጣን፣እውቀት ሳይኖረው ባለሙሉ እውቀት የሆነ ሰው ስብሃት ነጋ ብቻ ነው።እንዲያውም ከዚያ አልፎ ሙሉ ሉአላዊነት ያለው ግለሰብ ነው።"ይሉናል ፕሮፌሰር መስፍን! ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በኢኮኖሚክስ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂ የሆኑት አቶ ስብሃት አሁን ባላቸው ጉልበተኛነት የሚያሰይም የእውቀት ባለቤት አይደሉም።ባለእውቀት ለመሰኘት የዲግሪ ቁጥር ወሳኝ ነው ባልላችሁም የፕሮፌሰር ምልከታ መሰረታዊነቱን ማስመር እፈልጋለሁ ። ይቀጥላሉ ፕሮፌሰር "....በሉአላዊነቱ የተጎናፀፈውን ስልጣን ሙሉ በሙሉ ይጠቀምበታል።ይቆጣኛል ወይም ይቀጣኛል ብሎ የሚፈራው የለም።ስብሐት ነጋ የሚፈራው ምንም ነገር የለም።" አዎን አቦይ ስብሃት በመንግሥት ውስጥ ያሉ ግዙፍ መንግሥት ናቸውና በሳቸው ላይ ህግ የለም።እሳቸው ግን በሌላው ላይ መተግበር የሚችሉት ህግ አላቸው። ካማራቸው ቤተክርስቲያን ያብጠለጥላሉ÷ቀሳውስት ይዘረጥጣሉ÷ጳጳስ ይሾማሉ፣ይሽራሉ!ሲሻቸው በቤተ ሙስሊሙ ጉዳዩ ከነጫማቸው ይገቡበታል ። መንግሥት ሰማእት ባስረሳቸው ምድራዊ ገነት ባለሰባት ኮከብ ቅምጥል ህይወት የሚኖሩት አቦይ ቀና ብለው የሚመለከቱት ትልቅ የላቸውም!ሁሉን አሽቆልቁለው ነው የሚመለከቱት! ባለፈው እሁድ መንግሥታቸው በሙስሊሙ እየፈፀመ ስላለው የመብት ረገጣ ከመነሻው ጀምሮ የደረሰውን በደል በጀብደኛነት ተናግረውታል።የሞላላቸው ዘበናይ ናቸውና ቢያወሩ የሚፈሩት የላቸውም። ከአሁን ወዲያ የወያነ መንግሥት ቢያንስ በሙስሊሙ ጉዳይ እጄን አላስገባሁም በሚለው ውሸቱን እንዳያዳርቀን አርክቴክቸሩ አቦይ እውነቱን አፍረጥርጠውታል!እናመሰግንዎታለን! በጃጀ አእምሮ፣በበዛ ቅንጦት አመለካከታቸው እየተሳከረ የሚቀባጥሩት ስብሃት ነጋ ኢስላም እንደሀይማኖት አላስፈላጊ መሆኑን ቢያወሩ የሚገርም አይደለም።ፈጣሪ ስልጣኑን እንዳካፈላቸው ከሚያስቡ ሰው የሐይማኖት መኖር አስፈላጊነት መደራደር ይቻላል?ያማ ቢሆን በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ ያለፉትን ሙከራዎች ሲያዘንቡ ባልታዘብን ነበር! ፕሮፌሰር መስፍን እንዳሉት "....ስብሃት ነጋ የተናገረው ነገር ትክክል ይሁን አይሁን ጉዳዩ አይደለም።ዋናው ነገር መናገሩ ነው።" ባለጊዜዎች ሆነው የዘጠና ሚሊዮን ኢትዮጵያዊ መብት እንዳሻቸው የሚያለቁጡት አቦይ ይህ የታሪክ አጋጣሚ ገሸሽ ሲልባቸው የሚከፍሏቸው ብዙ እዳዎች አሉባቸው። እኛም እንደዜጋና በተለይ እንደሙስሊም ለአቶ ስብሃት ነጋ የምንላቸው "መሆን ያለብንን አይንገሩን!እናውቀዋለን!እጃችሁን አንሱልን!አዳራሽ ሞልተው ሲያጨባጭቧቸው የነበሩ ሆድ አደሮች ሙስሊሙን አይወክሉም!እናንተው የፈጠራቿቸው አሻንጉሊቶቻችሁ ናቸው።በየእስር ቤቱ ያጎራችኋቸው ወኪሎቻችን በዜግነት ተምሳሌትነታቸው የሚኮራባቸው እንጂ ኢስላምን የሚያስጠሉ አይደሉም። አቦይ እርስዎ ጭቆናን በመፋለም ሽፋን ያነፁት ተቃዋሚ አንጃ (ወያነ) በመቶ ሺህ ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ህይወት መቅሰፍት፣ለኤርትራ መገንጠል÷ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ መድቀቅ፣ለቢሊዮን ዶላሮች እዳ÷ ለማይታረቅ የብሄርተኛነት ጦስ እና የመሳሰሉት ቀውሶች ዳርጎናል። እያወገዟቸው ያሉት የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊዎች ደግሞ በተቃራኒው በዜጎች መካከል መከባበር÷መብትን በሰላማዊ መንገድ የመጠየቅ ስልጣኔ ያስተማሩ÷በአስሮች ሚሊዮን ተከታያቸው ጉልበት ሳያመፃደቁ ሰላምን ብቻ የሰበኩ ድንቆች ናቸው!! በኢትዮጵያዊው አእምሮ ያለውን እውነት ለመረዳት እርስዎና አንድ አቡበከር አህመድ ወይም እስክንድር ነጋ አደባባይ ውጡ። መልሱን ያገኙታል።
"አይ ስብሐት ነጋ!" በማለት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም የፃፉት አርቲክል እኚህን ጉምቱ የወያነ መንፈሳዊ አባት በአግባቡ ገልጿቸዋል ።
ቃል ከቃል አዋደን፣አረፍተ ነገሮች ብናዳቅል ፕሮፌሰሩ አቦይ ስብሀትን ፍንትው አድርገው እንዳሳዩን የማመላከት ብቃት አይኖረውም።
"....በኢትዮጵያ ስልጣን ሳይኖረው ባለሙሉ ስልጣን፣እውቀት ሳይኖረው ባለሙሉ እውቀት የሆነ ሰው ስብሃት ነጋ ብቻ ነው።እንዲያውም ከዚያ አልፎ ሙሉ ሉአላዊነት ያለው ግለሰብ ነው።"ይሉናል ፕሮፌሰር መስፍን!
ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በኢኮኖሚክስ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂ የሆኑት አቶ ስብሃት አሁን ባላቸው ጉልበተኛነት የሚያሰይም የእውቀት ባለቤት አይደሉም።ባለእውቀት ለመሰኘት የዲግሪ ቁጥር ወሳኝ ነው ባልላችሁም የፕሮፌሰር ምልከታ መሰረታዊነቱን ማስመር እፈልጋለሁ ።
ይቀጥላሉ ፕሮፌሰር "....በሉአላዊነቱ የተጎናፀፈውን ስልጣን ሙሉ በሙሉ ይጠቀምበታል።ይቆጣኛል ወይም ይቀጣኛል ብሎ የሚፈራው የለም።ስብሐት ነጋ የሚፈራው ምንም ነገር የለም።"
አዎን አቦይ ስብሃት በመንግሥት ውስጥ ያሉ ግዙፍ መንግሥት ናቸውና በሳቸው ላይ ህግ የለም።እሳቸው ግን በሌላው ላይ መተግበር የሚችሉት ህግ አላቸው።
ካማራቸው ቤተክርስቲያን ያብጠለጥላሉ÷ቀሳውስት ይዘረጥጣሉ÷ጳጳስ ይሾማሉ፣ይሽራሉ!ሲሻቸው በቤተ ሙስሊሙ ጉዳዩ ከነጫማቸው ይገቡበታል ።
መንግሥት ሰማእት ባስረሳቸው ምድራዊ ገነት ባለሰባት ኮከብ ቅምጥል ህይወት የሚኖሩት አቦይ ቀና ብለው የሚመለከቱት ትልቅ የላቸውም!ሁሉን አሽቆልቁለው ነው የሚመለከቱት!
ባለፈው እሁድ መንግሥታቸው በሙስሊሙ እየፈፀመ ስላለው የመብት ረገጣ ከመነሻው ጀምሮ የደረሰውን በደል በጀብደኛነት ተናግረውታል።የሞላላቸው ዘበናይ ናቸውና ቢያወሩ የሚፈሩት የላቸውም።
ከአሁን ወዲያ የወያነ መንግሥት ቢያንስ በሙስሊሙ ጉዳይ እጄን አላስገባሁም በሚለው ውሸቱን እንዳያዳርቀን አርክቴክቸሩ አቦይ እውነቱን አፍረጥርጠውታል!እናመሰግንዎታለን!
በጃጀ አእምሮ፣በበዛ ቅንጦት አመለካከታቸው እየተሳከረ የሚቀባጥሩት ስብሃት ነጋ ኢስላም እንደሀይማኖት አላስፈላጊ መሆኑን ቢያወሩ የሚገርም አይደለም።ፈጣሪ ስልጣኑን እንዳካፈላቸው ከሚያስቡ ሰው የሐይማኖት መኖር አስፈላጊነት መደራደር ይቻላል?ያማ ቢሆን በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ ያለፉትን ሙከራዎች ሲያዘንቡ ባልታዘብን ነበር!
ፕሮፌሰር መስፍን እንዳሉት "....ስብሃት ነጋ የተናገረው ነገር ትክክል ይሁን አይሁን ጉዳዩ አይደለም።ዋናው ነገር መናገሩ ነው።"
ባለጊዜዎች ሆነው የዘጠና ሚሊዮን ኢትዮጵያዊ መብት እንዳሻቸው የሚያለቁጡት አቦይ ይህ የታሪክ አጋጣሚ ገሸሽ ሲልባቸው የሚከፍሏቸው ብዙ እዳዎች አሉባቸው።
እኛም እንደዜጋና በተለይ እንደሙስሊም ለአቶ ስብሃት ነጋ የምንላቸው "መሆን ያለብንን አይንገሩን!እናውቀዋለን!እጃችሁን አንሱልን!አዳራሽ ሞልተው ሲያጨባጭቧቸው የነበሩ ሆድ አደሮች ሙስሊሙን አይወክሉም!እናንተው የፈጠራቿቸው አሻንጉሊቶቻችሁ ናቸው።በየእስር ቤቱ ያጎራችኋቸው ወኪሎቻችን በዜግነት ተምሳሌትነታቸው የሚኮራባቸው እንጂ ኢስላምን የሚያስጠሉ አይደሉም።
አቦይ እርስዎ ጭቆናን በመፋለም ሽፋን ያነፁት ተቃዋሚ አንጃ (ወያነ) በመቶ ሺህ ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ህይወት መቅሰፍት፣ለኤርትራ መገንጠል÷ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ መድቀቅ፣ለቢሊዮን ዶላሮች እዳ÷ ለማይታረቅ የብሄርተኛነት ጦስ እና የመሳሰሉት ቀውሶች ዳርጎናል።
እያወገዟቸው ያሉት የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊዎች ደግሞ በተቃራኒው በዜጎች መካከል መከባበር÷መብትን በሰላማዊ መንገድ የመጠየቅ ስልጣኔ ያስተማሩ÷በአስሮች ሚሊዮን ተከታያቸው ጉልበት ሳያመፃደቁ ሰላምን ብቻ የሰበኩ ድንቆች ናቸው!!
በኢትዮጵያዊው አእምሮ ያለውን እውነት ለመረዳት እርስዎና አንድ አቡበከር አህመድ ወይም እስክንድር ነጋ አደባባይ ውጡ።
መልሱን ያገኙታል።

No comments:

Post a Comment