ኢህአዴግ ጨነቃት…

ለሀምሌ ሰባት ቀን ለሀምሌ ስላሴ፣
እስላም ክርቲያኑ በጎንደር በደሴ፣
ኡኡታ ሊያሰማ ካደባባይ ወጥቶ፣
ላይቀር ተቀጣጥራል በአንድነት ተጠርቶ፡፡
ይህንን የሰማች ኢህአዴግ እናቴ፣
(እዝች ጋ እንጀራ እናቴ ስለው የሆነ ነገሩ አልገጠም አለኝ እንጂ ከእጇ ለበላን ለጠጣን፤ እና ለተበላን ለተጠጣን ሁሉ …ኢህአዴግ እናቴ… ከሚለው ይልቅ እንጀራ ኢህአዴግ እናቴ… የሚለው ይሻላታል! ግዴለም በዛው አንቀጥለው….)
ይህንን የሰማች ኢህአዴግ እናቴ፣
ተጨንቃለች አሉ፣
ተጠባለች አሉ፣
ተጣባለች አሉ፣
መላ አጥታለች አሉ፣
እኛ ለርሷ ጊዜ ስንቱን አመት ሁሉ እንኳን ሰልፏንና ሰይፏን ችለን ኖረን ኖረን…
እርሷ ለአንዲት ሰልፍ ሲጨንቃት ደነቀን፡፡
(የመጨረሻው ስንኝ እንደ ፀጋዬ ቤት ተጀምሮ እንደ እኔ ቤት ነው ያለቀው… )
No comments:
Post a Comment