Thursday, September 19, 2013

4 የአየር ሀይል አብራሪዎች ግንቦት 7ትን ተቀላቀሉ

4 የአየር ሀይል አብራሪዎች ግንቦት 7ትን ተቀላቀሉ

su-27-military-jet-of-ethiopia
መስከረም ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ አየር ሀይል ውስጥ በማገልገል ላይ የሚገኙ አራት አብራሪዎች ፣ የበረራ አስተማሪዎች ስርአቱን ከድተው ግንቦት7ትን መቀላቀላቸው ታውቋል።
ከኢትዮጵያ አየር ሀይል በመለየት ግንቦት 7ትን መቀላቀላቸውን ለኢሳት ያረጋገጡት የበረራ ባለሙያዎች በአየር ሀይል ውስጥ የተንሰራፋውን ዘረኝነትና አድሮ ለርምጃው እንደገፋፋቸው አመልክተዋል።
በኢትዮጵያ አየር ሀይል ውስጥ ከዘረኝነትና አድሎው ባሻገር በሰራዊቱ ውስጥ የተስፋፋው ሙስና ተቋሙን ለቀው የነጻነት ታጋዮችን ለመቀላቀል እንዳስወሰናቸው ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ አየር ሀይል ውስጥ በአብራሪትና በበረራ አስተማሪነት ሲያገለግሉ ቆይተው ስርአቱን የተለዩት አራቱ የበረራ ባለሙያዎች ካፒቴን አክሊሉ መዘነ፣ ካፒቴን ጥላሁን ቱፋ፣ ካፒቴን ጌቱ ወርቁና ካፒቴን ቢንአም ግዛው ናቸው።
በ1998 ኣም በሶማሊያ ከእስላማዊ ህብረት ሀይሎች ጋር በተደረገው ውጊያ ተሰታፊ እንዲሁም በዳርፉር የሰራዊት ማስከበር ተልእኮ የዘመቱት እነዚህ የበረራ ባለሙያዎች ሁለቱ ለከፍተኛ ትምህርት ከተላኩት ቻይና ተመልሰው ትግሉን መቀላቀላቸውን ሲገልጹ ሁለቱ ደግሞ ከሳምንት በፊት ድሬዳዋ ከሚገኘው የአየር ሀይል ምድብ ተነስተው ስርአቱን መክዳታቸው ተመልክቷል።
በቅርቡ የመረጃ መኮንን የነበረው ሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ግንቦት7ትን መቀላቀሉን መዘገባችን ይታወሳል።
በአሁኑ ጊዜ በርካታ ወጣቶች ንቅናቄውን እየተቀላቀሉ መሆኑን የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። አንዳንድ እግረኛ የሰራዊት አባላትም ድርጅቱን እየተቀላቀሉና ለመቀላቀልም ጥያቄዎችን እያቀረቡ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ዋነኛ ጠላት ወያኔ ብቻ ነው!!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ዋነኛ ጠላት ወያኔ ብቻ ነው!!

26351fb59e29fb0a1375427042
September 19, 2013
የግንቦት 7 የፍትህ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በቅርቡ ከኢሳት ቴሌቪዥን ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ዋነኛው የኢትዮጵያ ብሔራዊና ዘላቂ ጥቅም ጠላት ወያኔ መሆኑን አስረግጦ ተናግሮ ነበር። ይህንን አባባል አንድ ተቃዋሚ ለተቃውሞ ያህል ወይም ስርዓቱን የሚጠላ አንድ ግለሰብ ስርአቱን ስለሚጠላዉ ብቻ እንደተናገረው አድርጎ አቃልሎ ማየት ትልቅ ስህተት ነው። ወያኔ ከፍጥረቱ ጀምሮ እስከአሁኑ ቅጽበት ድረስ በሀገራችን ላይ የፈጸመውን ደባ በቅጡ ያላዩ ሰዎች ይህ አባባል የተጋነነ ይመስላቸው ይሆናል። ኢትዮጵያ ዛሬም አንደ አገር የቆመችዉ በህዝቦቿ ታላቅነትና እንዲሁም ለታሪካቸው ባሳዩት ክብርና ብርታት ነዉ እንጂ እንደወያኔማ ቢሆን ኖሮ የኢትዮጵያ ህልውና አደጋ ላይ ከወደቀ ሰንብቷል።
ኢትዮጵያ የሚለውን ውብና ታሪካዊ የስም ለመጥራት እየተጸየፈ “የሀገራችን ህዝቦች” እያለ ሲጠራን የነበረው የወያኔዉ ሹም የንቀት አጣራር ወያኔዎች ከሀገሪቱ ስም ጋር ሳይቀር የገቡበትን ጠብ ያሳያል። ወያኔ አባቶቻችን ባቆዩልን ዳር ድንደር የሚደራር ብቻ ሳይሆን የአገራችንን መሬት ላብዕዳን እንካችሁ ያለ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት ነዉ። በወያኔ እንደባሪያ ፈንግሎ የሚገዛት አገራችን ኢትዮጵያን የታሪክ አጋጣሚ እጁ ላይ ጥሎለት ነዉ እንጂ እሱ እንደሚነግረን ወያኔ ከራሱና ከጉጅሌዎቹ ጥቅም አስበልጦ ኢትዮጵያን አስቧት አያውቅም።
መገነጣጠል ግብ እንዲሆን በህገ መንግስት ደረጃ አንቀጽ ጽፎ ያስቀመጠው ወያኔ እሱ እንደሚለዉ ለብሔረሰቦች መብት አስቦ ሳይሆን ኢትዮጵያ አልዘረፍ ካለችን በትነናት ብንሄድስ ከሚል አላማ መሆኑን ሌናጤን ይገባል። ከምር ለብሄረሰቦች መብት በመቆርቆር ቢሆን ኖሮ ከጠመንጃና ከፍጅት በፊት የብሄረሰቦችን መብትና ነጻነት አክብሮ እራሳቸዉን በራሳቸዉ እንዲያስተዳድሩ ይተዋቸዉ ነበር።።
ወያኔ ኢትዮጵያን የሚፈልጋት ለርሱና ለጋሻ ጃግሬዎቹ የወርቅ እንቁላል የምትጥል ዶሮ ሆና ስላገኛት ብቻ ነው። ሀገሪቱን እያለማሁ፣ እያሳደግኩ ነው የሚለው ዲስኩር ለተራ መደለያ እንኳን የማይሆን ውሸት ለተራበው ህዝብ ምኑም እንዳልሆነ ያውቀዋል።
የሀገሪቱን ለም መሬት በሄክታር ባንድ ፓኮ ሲጋራ ዋጋ የሚቸረችረው ወያኔ እነዚህ ባእዳን በጎን የሚሰጡትን የሀገራችንን መሬት ዋጋ ኪሱ መክተቱን አረጋግጦ ነው። ዛሬ በመላ ሀገሪቱ የሚነዛው የኬሚካል ማዳበሪያ በጥቂት አመታት ውስጥ የሀገሪቱን አፈር ድራሽ እንደሚያጠፋ ወያኔ የአዋቂዎች ምክር ሳይሰማ ስለቀረ አይደለም። በአጥፊ ስራው የቀጠለው መዝረፍ የሚችለዉን ንብረት ካጋበሰና ከዘረፈ በኋላ ነገ ኢትዮጵያ እንደአለ ባድማ ብትሆን ቅንጣት ስለማይሰማዉ ነዉ። ለሀገር የሚያስብ መንግስት ቢሆን ኖሮ የአገሪቱ ወጣትና የተማረ የሰዉ ኃይል እንደ ጎርፍ ከአገሪቱ እየጎረፈ ሲወጣ ይቆረቆር ነበር። ወያኔ የተማረ ሰው ቢሰደድ፣ ዜጎች ቢራቡና በገዛ አገራቸዉ ቢዋረዱ ጉዳዩ አይደለም። በሰላማዊና ህገመንግስታዊ መንገድ ጥያቄ ያነሳን ዜጋ ሁሉ እንደአውሬ የሚቀጠቅጠውና ወህኒ ቤት የሚያጉረው ይህ በደል ነገ በሀገሪቱ ዘላቂ ህልውና ላይ የሚያመጣውን መዘዝ አጥቶት አይደለም። የአገራችን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም ጉዳዩ ስላልሆነ እንጂ።
የኢትዮጵያን ብሄር ቤሄረሰቦች የሚያይዟቸውን በሚሊዮን የሚቆጠሩ የአንድነት ክሮች እያንቋሸሸና እንደሌሉ እየሰበከ በሚለያዩንን ጥቃቅን ውጭያዊ የቋንቋና የዘር ግንዶች አጉልቶ የሚያሳየን አገራችንንና ህዝቧን እንደ አንድ ሀገር ሳይሆን እንደጊዚያዊ የዝርፊያ ቀጠና ስለሚመለከት ብቻ ነው።
ወያኔና ሎሌዎቹ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም ጠላቶቹ ናቸው እያሉ አንዴ የፈረሰችዉ ሶማሊያን፤ ሌላ ጊዜ ወደ ኤርትራና ግብጽ ጣቱን የሚጠነቁሉት አይናችንን ከወያኔ ላይ እንድናነሳ ነዉ እንጂ ከወያኔ በላይ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም ጠላት የለም። ወያኔ በአካል እኛን ከሚመስሉ ኢትዮጵያውያን መሃል ይውጣ እንጂ፣ በተግባር ከቀን ጅብ ያልተናነሰ የዘረኞችና የዘራፊዎች ቡድን ነው። ብዙ ጊዜ ወያኔ ራሱ የጻፈውን ህግ ሲጥስ ለምን ብለን የምንገረም አለን። ወያኔ ሕግና ሕገ-መንግስት፣ ለአገራቸዉ የሚቆረቆሩ ምሁራንን የሚያፈሩ የትምህርት ተቋማት፣ በህዝብ የሚታመን ሰራዊት፣ ለህግ ብቻ የሚሰራ ፍርድቤትና የመሳሰሉት ዘላቂ ተቋማት እንዳይኖሩን የሚያደርገውና ያሉትንም የሚያፈርሰው ለኢትዮጵያ ብሄራዊና ዘላቂ ጥቅም ምንም ደንታ ስለሌለዉ ነዉመሆኑን የሚዘነጋ ኢትዮጵያዊ በእጅጉ የዋህ ነው። ወያኔ የኢትዮጵያ ጠላት ነው።
ስለዚህም እንላለን እኛ የግንቦት 7 ልጆችህ ሀገርህ ትውልድ ተሻግራ እንድትቀጥል አንተም የምትኮራባት ዜጋ እንድትሆናት የምትሻ የኢትዮጵያ ልጅ ሁሉ ሀገርህን ከወያኔ የቀን ጅቦችና ወራሪዎች አድን። አጎንብሰህ ሳይሆን ቀና ብለህ የምትሄድባት ሀገር እንድትኖርህ የምትሻ ሁሉ ለማይቀረው የጀመርነውን የአርበኝነትና የነጻነት ትግል ጉዞ ተቀላቀለን። እኛ የተባበርን እለት አብረን የተነሳንና በቃ ያልን እለት ታሪካዊቷ ሀገራችንና ታላቁ ሕዝባችን ዘላቂ ብሄራዊ ጥቅማቸው ይከበራል።
አዎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ዋነኛ ጠላት ወያኔ ብቻ ነው!!

Tuesday, September 17, 2013

የርዕዮት አለሙ የስር ቤት አያያዝ CPJ

የርዕዮት አለሙ የስር ቤት አያያዝ CPJ

0,,6248441_4,00
Reeyot_Alemu_emf
ቀን 17.09.2013
የወጣት ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ የእስር ቤት አያያዝ እየተባባሰ እንጂ እየተሻሻለ አለመሆኑ ተሰማ።
ወላጅ አባቷና ጠበቃዋ እንደሚሉት የጠያቂዎቿ ቁጥር ቀንሷል፣ የእስር ቤት አልጋዋንም ለሌላ እስረኛ እንድትለቅ ተገዳለች። በሌላ በኩል ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ሴቶች ድርጅት እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማትም ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ ያለአንዳንች ቅድመ ሁኔታ እንድትፈታ እየጠየቁ ነው። «ባልፈጸመችው ወንጀል ይልቁንም በመብት ተሙዋጋችነትዋ በእስር ቤት ያውም ኢሰብኣዊ በሆነ አያያዝ እየማቀቀች የምትገነው ወጣት ጋዜጠና ርዕዮት አለሙ» ይላል ዓለም ዓቀፉ የኢትዮጵያ ሴቶች ድርጅት በምህፃሩ IEWO ባለፈው ዓርብ ባወጣው መግለጫ ለበርካታ ኢትዮጵያት ሴቶችም መልካም አርዓያነት መጠቀስ ከጀመረች ከራርማለች።
ከዚሁ የተነሳ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እና ዓለም ዓቀፍ የመብት ተሟጋቾች ሁሉ ይህንኑ በመቃወም ርዕዮት ዓለሙን ጨምሮ ሌሎችም በግፍ ታስረው በእስር ቤት እየተሰቃዩ ናቸው ያላቸው እስረኖች ይፈቱ ዘንድ እንዲተባበሩ ዓለም ዓቀፍ ጥሪ ኣቅርበዋል። ርዕዮት አለሙ በዘመናችን ወደር በሌለው ጀግንነት ከሚወደሱት ጥቂት ኢትዮጵያን መካከል ትጠቀሳለች ያለው ድርጅቱ ለመፃፍ ነፃነቱዋ እና በኣጠቃላይ በመብት ተሟዋጋችነቱዋ በምትከፍለው መስዋትነት ሁሉ ድጋፋችን እንደማይለያት እናረጋግጣለን ብለዋል።
CPJ የተሰነው የጋዜጠኖች መብት ተሟጋች ድርጅትም እንዲሁ የእስር ቤቱ ኣያያዝ እንዲሻሻል ከመጠየቁም ባሻገር ርዕዮት ዓለሙን ጨምሮ እስክንድር ነጋ እና ሌሎችም ያለኣንዳች ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ኣሳስበዋል። ያም ሆኖ በእስር ቤቱ የእስረኖች ኣያያዝ እየተባባሰ እንጂ እየተሻሻለ ኣለመሆኑን ነው ዘገባዎች የሚጠቁሙት በተለይም ርእዮት አለሙን የሚጎበኑ ሰዎች ቁጥር መቀነሱን በመቃወም ከመስከረም 1 – 5 ድረስ የረሃብ አድማ ማድረጉዋን ወላጅ አባትዋ እና ጠበቃዋ አቶ ዓለሙ ጎቤቦ ዛሬ ለዶቸቤሌ ኣስረድተዋል።
የጋዜጠና ርዕዮት አለሙ ጤንነት በመልካም ሁኔታ ላይ መሆኑን እና ሞራልዋም ቢሆን ብርቱ መሆኑን የገለጹት አቶ አለሙ የኣመክሮ መብትዋን ተጠቅማ ከወህኒ ቤቱ እንዳትፈታም በለስልጣናቱ ከወዲሁ በሰበብ ኣስባቡ ሴራ እየጠነሰሱ ነው በማለት ይወቅሳሉ።
ጋዜጠና ርዕዮት አለሙ በአወዛጋቢው የጸረ ሽብር ህግ ተከሳ የታሰረችው በሰኔ ወር 2003 ዓ ም ሲሆን በተያዘባት የወንጀል ጭብጥ የ14 ዓመት እስራት ከተበየነባት በሁዋላ በይግባን ወደ 5 ዓመት ዝቅ ብሎላታል ከዚህ ሁሉ ሂደት ጋርም ጋዜጠና ርእዮት ዓለሙ ባለፈው ዓመት የ2013 የዓመቱ ምርጥ ጋዜጠና ተብላ በ ዓለም ዓቀፉ የትምህርት እና የባህል ተቐም UNESCO ኣማካንነት ዓለም ዓቀፍ የፕሬስ ነጻነት ሽልማት ማሸነፍዋ ይታወሳል።

መስከረም ሲጠባ አደይ ሲፈነዳ ……(አቶ ይድነቃቸው ከበደ)

መስከረም ሲጠባ አደይ ሲፈነዳ ……(አቶ ይድነቃቸው ከበደ)

Yidenachew-Kebede
September 17, 2013
መስከረም ሲጠባ አደይ ሲፈነዳ ……………….
የዘመን መለወጫ ክብረ በዓል በየትኛውም አገር እንደ አገሩ ወግና ልማድ በድቅመት የሚከበር በዓል ነው፤በእኛ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ደግሞ ልማድና ወጋቻን እጅግ ከመጠንከሩ የተነሳ ለአዲስ ዓመት ወይም ለዘመን መለወጫ ክብረ በዓል ዝግጅታችንም ሆነ አከባበራችን እጅግ በጣም ጠንካራና ደስ የሚል ነው፡፡አዲስ ዓመት የሁሉ ነገር መጀመሪያ ነው ለዚህም ነው ብዙ እቅዶቻችን ከመስከረም ወር የሚጀምረው፤ያቀድነው ነገር በዓመቱ መጨረሻ ሊሳካ ወይም ላይሳካ ይችል ይሆናል ቁም ነገሩ ግን በዓመቱ መጀመሪያ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ለማሳካት የታሰበ እቅድ መኖሩ ነው፤ለእቅዱ አለመሳካት ውጫዊና ውስጣዊ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ እነዚህን እንቃፋት የሆኑ ምክንያቶች ለይቶ ማወቅ በራሱ የእቀዱ አንድ አካል በማደረግ እንደገና ለመጪው አዲስ ዓመት ለተሸለ እቅድ ግባት ይሆናል፡፡semayawi pary, ydneqachew kebede
የዘንድሮ አዲስ ዓመት ከግለሰባዊ ፋይዳ በላይ አገራዊና ህዝባዊ የለውጥ ፋይዳ የበዛ እንደሚሆን ምልክቶቹ አብዝተው ይታያሉ፤እነዚህ ምልክቶች ከባለፈው ዓመት ለዘንድሮዎ የተሸጋገሩ የለውጥ ምልክቶች ናቸው፤በመሆኑም ለለውጥ የተነሳሳው ለወጥ ፈላጊ ለውጡኑ የሚያከሽፍበት አንዳችም ምክንያት ስለመኖሩ እጠራጠራለው ክሽፈት ቢያጋጥም እንኳን ወድቆ ለመነሳት ብዙ ጊዜ የሚባክን አይመስለኝም ፡፡
መውደቅ መነሳት ከሚንቀሳቀስ ነገር የሚጠበቅ ክስት ነው መንቀሳቀስ ደግሞ በሀገር ውስጥና በውጪ በሚገኙ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን፣ ፖለቲከኞች፣ በአይማኖት ተቋመት፣በሲቪክ ማህበራት እና በመሳሰሉት እንቅስቃሴው መሰልቸትና ድካም የማይታይበት ጠንካራ እንቅስቃሴ ነው፤ይህ እንቅስቃሴ ከባለፉት ወድቆ መነሳት እንቅስቃሴ ት/ት የተቀሰመበት ስለመሆኑ ከምልክቶቹ መካከል አንዱ ነው፡፡
በአገራችን ለለውጥ የሚገፋፉ ብዙ ምክንያቶች መኖራቸው የሚታወቅ ቢሆንም ከብዙ ምክንያቶች በዋንኝነት ትኩረትን የሚስቡት የለውጡን አይቀሪነት አሳበቂ ምክንያቶች ከሆኑት ውስጥ፡-
1ኛ. በዓለም ላይ ካሉ ታላላቅ እምነቶች መካከል ክርስትና እና እስልምና ዋንኞቹ ናቸው፤እነዚህን እምነቶች በመቀበል እኛ ኢትዮጵያዊያን ከቀዳሚዎቹ መካከል እንገኛለን ክርስትናን እና እስልምና እምነትን መቀበላችን ብቻ ሣይሆን የተቀበልነው እምነት ህግና ሥርዓት አክብሮ በማስከበር ወደር አይገኝልንም፡፡ይሁን እንጂ መንግስት በልማት ስም የአምልኩ ቦታዎችን በመጋፋት ቤተ ክርስቲያንን ተዳፍሯል፤ይህ ነገር ተገቢ አይደለም ያሉ የሃይማኖት አባቶች ተደብድበዋል፣ተገለዋል እንዲሁም ከአገር ተሰደዋል፡፡
መንግስት በሃይማኖት ሃይመኖት በመንግስት ጣልቃ አይገባም የሚለውን ህገ-መንግስታዊ ድንጋጌ መንግስት በመጣስ በሙስሊም እምነት ዘው ብሎ በመግባት የእመንቱን መሪዎች እስከመምረጥ ደረጃ ተደርሷል፤ ይህን አይቶ ዝም አለማለት እስላማዊ ግዴታ እንደመወጠት የቆጠሩ እንቢ ለእምነቴ ያሉ በእስር እና በስቃይ ላይ ይገኛሉ፡፡ በእነዚህ ታላላቅ እምነቶች መንግስት እጁን በማስገባት የፖለቲካ ዓላማ ማስፈፀሚያ ለማድረግ ያልፈነቀለው ድንጋይ ምን አለ? በተለይ በሙስሊሞች ላይ እተየፈፀመ ያለው በደል እና በእምነቱ ተከተዮች የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ላይ ያለጥፋታቸው በሐሰት በመወንጀል አሸባሪ ብሎ በእስር ማሰቃየቱ እጅን ጨብጦ ጥርሱን ነክሶ ያልተቆጨ ማነው ?
2ኛ. ኢትዮጵያ አገራችን የብዙ ሺህ ዓመት አኩሪ ታሪክ ያላት እና የተለያዩ ንዎች የሚነገርባት ህዝቧ የቋንቋ ልዩነት ሣይገድበው አንዱ ከሌላው የተዋለደባት እጅግ ውብ እና ማራኪ ን፣ብህል ፣ልምድ ፣ወግ ፣አለባበስ እና አመጋገብ ወዘተ….. የሚታይባት ድንቅ አገራችን ናት፡፡ ይሁን እንጂ የኢህአዴግ መንግስት ይህ ቦታ የናተ አይደለም በማለት ዜጎችን በማፈናቀል ሀብትና ንብረት በማውደም ጎጠኝነትና ዘረኝነት በማስፋፋት ላይ ይገኛል፤እንዲህ አይነቱ አሳፋሪ ተግባር በአገራችን በአራቱም አቅጣጫ በዘመቻና በእቅድ በመንግስት የተፈፀመ ህገወጥ ተግባር ነው፡፡በመሆኑም ከኢትዮጵያዊነት በላይ መንደረኝነት እንዲነግስ በመንግስት እየተደረገ ያለው ዘመቻ ያላስቆጨው፣ ያላንገበገበው ማነው ? ይህን ቁጭቱን እና በደሉን ለመግለፅ ጊዜና አጋጣሚውን እየጠበቀ ያለው ስንቱ ነው ?
እኛ ኢትዮጵያዊያን በእድሜና በውቀታቸው ከፍ ላሉ ሰዎች ያለን ከበሬታ እጅግ የላቀ ነው ፤ለዚህም ነው ለሽምግልና ጉዳይ ቶሎ እጅ የምንሰጠው በሽምግልና ካጣነው ነገር በላይ ያተረፍነው የበዛ ነው ፡፡ ይሁን እንጂ የቆየውና ጠቃሚ የሽምግልና ወገና ሥርዓት በመጠበቅ የአፋር ፣ የኦሮሚያ ፣ የጋምጎፋ (ቆጫ ወረዳ) እና የሲዳማ የአገር ሽማግሌዎች በአካባቢያቸው ለታየው አስተዳዳሪያዊ ችግር መፍትሔ ለመሻት ከታችኛው የአስተዳደር አካል እስከ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያደረጉት ጥረት ውጤት አልባ ነበር፤ ከምንምንም በላይ የሽምግልና ክብር በመጋፋት መንግስት ጠቃሚ የሆነውን ወግና ሥርዓት ለመናድ የሄደበት መንገድ ሽማግሌዎችንና የተወከሉበትን ማህበረሰብ ምን ያህል ነው ያስከፋው ?
3ኛ. ‹‹ በኑሮ ውድነት የጎበጠው ትከሻችን እረፍት ይሻል ›› ኑራችን አላምር ሲል መፈክራችን ማማሩ የሚገርም ነው ! ይህ መፈክር ሰማያዊ ፓርቲ በአዲስ አበባ ባካሄደው የተቃውሞ ሠልፍ ከፍ ብሎ የተሰማ ጥያቄ ነወ፤ እውነትም አብዛኛው ኢትዮጵያዊ የኑሮ ውድነት ትከሻውን ከማስጉበጥ አልፎ ህይወቱን እየነጠቀወ ነው፡፡ ባለ ሁለት ሃአዝ እድገት በመንግስት ተደጋግሞ የሚነገር አስማታዊ እድገት ምግብም መጠጥም አልሆን ብሎ በመንግስት የሚነገረው እድገትና የምንኖረው ሕይወት ሆድና ጀርባ ሆኖ አልገጥም እያለ ተቸግረናል፡፡
የስራ አጥነት ቁጥሩ በጣም የበዛ ነው፣ሰራተኛም ሰርቶ የሚከፈለው ወራዊ ደሞዝ ወሩን ሙሉ የሚያቆይ አይደልም፣ በኑሮ ውድነቱ ምክንያት 2.5 ሚሊዩን ዜጎች ለጎዳና ተዳዳሪነት መዳረጋቸው የመንግስት መስሪያ ቤት የሆነው የማህበራዊ ዋስትና ድርጅት ባስጠናው ጥናት መሰረት ይፋ አድረጎኃል፤ጎዳና ያልወጡ እቤታቸው ጎዳና የሆነባቸው ዜጎች ቤት ይቁጠራቸው፡፡
በመሆኑም እንዲህ አይነቱ ምስቅልቅል የበዛበት የኑሮ ውድነት ዋንኛው መንስሄ ብልሹ የመንግስት አስተዳደር ስለመሆኑ የእኛ መንገስትና ኑራችን ዋንኛ ማስረጃ ነው፤ስለሆነም እንዲህ አይነቱ ብልሹ የመንግስት አስተዳደር አቅፎና ደግፎ ይዞ የሚሄድ ጉልበትም ሆነ አንጀት ከወዴት ይምጣ ?
4ኛ. አሁን ያለው የአባገነን ሥርዓት የተረጋጋና ጉልበት አልባ መሆኑ ሌላኛው የለውጡን አይቀሪነት አሳበቂ ምክንያት ነው፡፡ ከእሳቸው ሞት በፊት ይታይ የነበረው የአንድ ሰው ፈላጭ ቆራጭነት ከእሳቸው ሞት በኃላ የስርዓቱ ፊት አውራሪዎች ከመብዛታቸውም በላይ በቡድን የተከፈሉና እኛ እናተ መባባላቸው ከጥጋባቸው በላይ የስልጣን ጥማታቸውን የሚያሳይ ነው፤ ግን በሁለት ሆዳሞች መሃል እህል ይደፋል እንጂ ማንም አይበላውም፡፡
ሌላው የስርዓቱ የፊት ሰዎች ከውስጣዊ ሹኩቻ ባለፍ በአደባባይ አንዱ ለሌላው በሙስና እና በስልጣን መባለግ ስም ማሰርና መክሰስ ሌላኛው አገር ጥሎ መሄድ መሳ ለመሳ እየተካሄደ ያለ ውስጣዊ ሹኩቻ ነው፤በእንዲ መልኩ በውስጥ የተወጠረው የአባገነን ስርዓት በተጠናከረ እና ሠላማዊ በሆነ ህዝባዊ ግፊት ፈንድቶ ውስጣዊ ሰንኮፉ የማይነቀልበት ምክንያት ምንድነው ?
5ኛ. ሐሳብን በነጻ የመያዝና የመግለጽ እንዲሁም የመደራጀት መብት ዓለም አቀፍ እንዲሁም ሕገ መንግስታዊ መብት ነው፡፡በመሆኑም አንዱአለም አራጌ፣ ናትናሄል መኳንን፣ በቀለ ገራባ፣ ኦልባና ለሊሳ እና ሌሎችም የፖለቲካ እስረኞች እንደማንም ኢትዮጵያዊ የራሰቸው ኑሮ እና ህይወት ያላቸው ናቸው፤ ይሁን እንጂ ነፃነት እና ፍትህ ለነሱ ሁለተኛ ጉዳይ አይደለም የመጀመሪያ ጥያቄያቸው ነው ! ከራስ ወዳድነት አልፈው ይህ ጥያቄ የኛ ብቻ ሣይሆን የኢትዮጵያዊያን ጥያቄ ነው በማለት በአደባባይ ስለነፃነት እና ፍትህ የዘመሩ በዚህም አኩሪ ተግባራቸው በእኛ የኢትዮጵያዊያን ዘንድ ልዩ ቦታ የምንሰጣቸው ነን፡፡የታሰሩበት እና የሚሰቃዩበት ጉዳይ የኛም ጉዳይ ነው የሚሉ ቁጥራቸው መብዛቱ ሠላማዊ ትግሉ አባገነን ስርዓቱን የሚበላ እሳት መሆኑ ማሳያ ነው፡፡
ይህ በእንዲ እንዳለ በአገር እና በህዝብ ላይ የሚፈፀም በደል ማቆም አለበት መንግስት እየወሰዳቸው ያለው እርምጃ የዜጎች ሰብአዊ እና ዲሞክራሳዊ መብቶችን የጣሱ ናቸው፤ በማለት ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብታቸውን ተጠቅመው ከምንም በላይ የጋዜጠኝነት ስነ-ምግባር ጠብቀው ሚዛናዊ መረጃ ለእዝብ ያደረሱ ዓለም ዓቀፍ ተሸላሚ የሆኑ ጋዜጠኖች በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ እርዮት ዓለሙ እና ውብሸት ታዬ በስራቸው ዓለም ያደነቃቸው አድናቆቱም በሽልማት የታጀበ መሆኑ ለማናችንም ግልፅነው፡፡ይሁን እንጂ እነዚህ የዓለም ህዝብ ቆሞ ያጨበጨበላቸው ጋዜጠኞች አባገነኑ መንግስት በሽብርተኝነት ወንጅሎ በማሰር እያሰቃያቸው ይገኛል ፡፡ ይህ ስቃያቸው ያልተሰማው ማነው ? ከዚህ ስቃይ እንዲወጡ ምን ባደርግ ይሻላል እያልን እራሳችንን ያልጠየቅን ስንቶቻችን ነን ? በሆነውስ ነገር ያልተቆጨ ማነው ?
6ኛ. በውጪ የሚገኙ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተፅኖ ሌላው ለአባገነኑ ሥርዓት የእግር እስታ መሆን ነው፤ በውጪ የሚገኙ ዜጎች በአገር ውስጥ ለታየው ብሉሹ አስተዳደር ፊት ከመንሳት ባለፈ በተደራጀና በሚያስደንቅ ሁኔታ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ነው፡፡ እንቅስቃሴውም ከሌላው ጊዜ በተሸለ በኢኮኖሚ እና በፖለቲካው ስኬታማ መሆኑ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ በተለያየ ወቅት በሰጡት ቃለ ምልልስ እና መንግስት በሰጠው መግለጫ በውጪ በሚገኙ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን መንግስት መሸነፉን የሚያሳብቅ ነው፡፡
በመሆኑም ከላይ በማሳያነት የቀረቡ የለውጡ ግፊት ሃይል ከሆኑ ምክንያቶች ውስጥ የተጨለፈ ቢሆንም በመንግስት የአስተዳደር ብሉሹነት ምክንያት ይህ አስተዳደር በቃኝ ለማለት ምክንያቱ ብዙ ነው፡፡ ስለሆነም መስከረም ሲጠባ አደይ ሲፈናድ ለውጥ ፈላጊ የፈለገውን ለውጥ ላለማጣት ከባለፈው ዓመታት ት/ት በመውሰድ በዘንድሩ አዲስ ዓመት ከግለሰባዊ ፋይዳ በላይ አገራዊና ህዝባዊ ለውጦች የምናይበት ዓመት ይሆናል፡፡

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና ሌሎች በእስር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ ተጠየቀ።

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና ሌሎች በእስር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ ተጠየቀ።

1044303_169829796523576_1916727500_n
መስከረም ፮(ስድት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አዲስ ከዓመት በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ ለ14 ወራት በቃሊቲ እስርቤት ከታሰሩ በኋላ ተፈተው የወጡት ስዊድናውያን ጋዜጠኞች ማርቲን ሺቢ እና ዩዋን ፐርሹን እንዲሁም ዓለምዓቀፍ የሰብዓዊና የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅቶች ተወካዮች፡ ጋዜጠኞችና በስዊድን የሚኖሩ በመቶ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እና ስዊድናውያን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባዘጋጀው ደብዳቤ ላይ ፊርማቸውን በማኖር ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ የታሰሩ ጋዜጠኞችን እንዲፈቱ ጠይቀዋል።
ስዊድናውያን ጋዜጠኞች ኢትዮጵያ ውስጥ ያሳለፉትን የእስር ህይወት የሚተርከውን እና በቅርቡ ለህትመት የበቃው 438ቱ ቀናት የሚለው መጽሃፋቸው ኢትዮጵያውያንን የህሊና እስረኞችን ለማስታወስ በተዘጋጀው ዝግጅት ላይ ይፋ እንዲሆን የወሰኑት በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሰው በከፍተኛ ስቃይ ለሚንገላቱት ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች እና ሌሎች የህሊና እሰረኞች የገቡትን ቃል ለማደሰ እንደሆነ በዝግጅቱ ላይ ለተገኙ ተሳታፊዎች ገልጸዋል።
በአሸባሪነት ተወንጅለው በእስር ላይ የሚገኙ የስራ ባልደረቦቻቸው በዓለም ዓቀፉ ሚዲያ በመዘንጋታቸው እና ይሄንን በመላው ዓለም ዘንድ ትኩረት እያጣ የሚገኘውን ከጊዜ ወደጊዜ እየተባባሰ የመጣውን በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄደውን እጅግ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና አፈና እንዲቆም እርዳታ ለጋሽ አገሮች፡ አህጉራዊ እና ዓለምዓቀፍ ድርጅቶች በኢህአዴግ መንግስት ላይ ግፊት በማድረግ በቃሊቲ፡ በቂሊንቶ፡ ዝዋይ እና ሌሎችም እስርቤቶች የሚገኙ ጋዜጠኞች፡የተቃዋሚ ፖርቲዎች መሪዎች እና በሺህ የሚቆጠሩ ንጹሃን ዜጎች እንዲፈቱ ለማሰብ መጽሀፋቸውን በዝግጅቱ ላይ ይፋ ለማድረግ መወሰናቸውን ገልጸዋል።
የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር በህይወት ከተለዩ በኋላ በኢትዮጵያ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና አፈና ይሻሻላል ሲባል ጭርሱን ተባብሶ መቀጠሉን በመጠቆም በቅርቡ ከማርቲን እና ዩዋን ጋር በተመሳሳይ ወራት እና ወንጀል ታስራ አሁንም በቃሊቲ እስርቤት ከፍተኛ በደል እየተፈጸመባት ያለችውን ርዕዮት ዓለሙን እንደዓብነት አንስተዋል።
ርዕዮት በእስር ላይ በምትገኝበት በቃሊቲ ማረሚያ ቤት እየተፈጸመባት ያለውን ኢሰብዓዊና ኢህጋዊ በደሎች ለመቃወም ከመስከረም ፩ ጀምሮ በረሃብ አድማ ላይ መሆኗን በመጠቆም ይህ በገዥው ስርዓት ሎሌዎች በህሊና እስረኞች ላይ የሚካሄደው በደል እና ግፍ ቅጥ እያጣ መሆኑን አስታውቀዋል።
ከዚህ በተጨማሪም ውብሸት ታዬ ከእስር እንዲፈታ ያቀረበው የይቅርታ ደብዳቤ በገዥው መንግስት ተቀባይነት ካለማገኝቱም ባሻገር ከአራት ወራት በፊት ከቂሊንጦ ወደ ዝዋይ እስርቤት ሆን ተብሎ በመዛወሩ ልጁ እንዲሁም እድሜያቸው ከሰማኒያ ዓመት በላይ የሆናቸው ወላጆቹ ተመላልሰው ሊጠይቁት እንዳልቻሉ ተገልጿል።
ኤቢፍ የተባለው የስዊድን የሲቪክ ተቋም፡ አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ድንበርየለሹ የጋዜጠኞች ማህበር በስዊድን መስከረም 4፣ 2006 ዓም የተካሄደውን ዝግጅት በጋራ በመሆን ማዘጋጀታቸውን ቴዎድሮስ አረጋ ከስቶክሆልም ዘግቧል።
በሌላ ዜና ደግሞ መንግስት በስዊድን ስቶክሆልም ያዘጋጀው የቦንድ ሽያጭ መርሀግብር በተቃውሞ እንዲጨናገፍ ተድርጓል።
በኢትዮ ስዊድን መርሃግብር አስተባባሪነት ከጎትምበርግና ስቶክሆልም የተሰባሰበዉ የተቀዋሚ ኃይል የአዳራሹን መግቢያ በሰዉ በመዝጋትና የራሳቸዉን ቀስቃሽ ሙዚቃዎችን በማጫወት የአዳራሹን መግቢያና አካባቢዉን ተቆጣጥረዉት ስለነበር ይህን ጥሶ የሚገባ ባለመኖሩ አዳራሹ ከቦንድ አዘጋጆች በቀር ባዶዉን እንዲዉል መደረጉን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
በምሽቱ የሙዚቃ ፕሮግራም ላይ በተፈጠረ ረብሻም የሙዚቃ ዝግጅቱ እንደተጠበቀው አለመካሄዱን መረጃው አመልክቷል። በስዊድን መንግስት ያዘጋጀው የቦንድ ሽያጭ ሲከሽፍ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።

734 ሚሊዮን 600 ሺ ብር የመዘብሩ የስራ ሃፊዎች አለመቀጣታቸውን መረጃዎች አመለከቱ

734 ሚሊዮን 600 ሺ ብር የመዘብሩ የስራ ሃፊዎች አለመቀጣታቸውን መረጃዎች አመለከቱ

576820_643438789017118_1777115518_n
መስከረም ፮(ስድት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አዲስ ከስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሺን የተገኝው መረጃ እንደሚያመለክተው ከተለያዩ የፌደራል መስሪያ ቤቶች 734 ሚሊዮን 6 መቶ ሺ ብር የመዘብሩ የስራ ሃፊዎች በተጣራ መረጃ ክስ ቢመሰረትባቸውም የውሳኔ ቅጣት እንዳልተላለፈባቸው ታውቋል።
ለረጅም ጊዜ በተደረገ ምርመራ ተጣርቶና መስረጃ ተገኝቶባቸው ከ2004 ዓም ጀምሮ ክስ የተመሰረተባቸው የተለያዩ የሙስና ወንጀሎች የውሳኔ ሀሳብ እንዳልተላለፈባቸው ከመሰሪያ ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ላይ 94 ሚሊዮን 300 ሺ ብር ከትምህርት ተቋማት ግንባታ ጋር በተያያዘ የተፈጸመ የሙስና ወንጀል ምርመራ ተጠናቆ ክስ ቢመሰረትም በቂ ውሳኔ ሳያገኝ ቀርቷል።
ከአራዳ ክ/ከተማ መልሶ ማልማት ፕሮጀክት ጋር በተያያዘ ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ ህገወጥ የካሳ ክፍያ በመፈጸሙ ሦስት የምርመራ መዝገቦች ተጠናቀው በ2004 ዓ.ም ክስ ቢመሰረትም የቅጣት ውሳኔ አላገኝም።
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሀራጅ ሽያጭ ጋር በተያያዘ የ12 ሚሊዮን ብር እና የ34 ሚሊዮን ብር ህገወጥ ብድርን እንዲፈፀም ያደረጉ አካላት በቂ የሰነድ ማስረጃ እንደተገኘባቸው ቢገለጽም እርምጃ ሳይወሰድ ቀርቱዋል፡፡
በቀድሞው የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ከመመሪያና አሰራር ውጪ ለግለሰቦች የስልክ መስመር እንዲዘረጋ በማድረግ በህገወጥ መንገድ ወደ ውጭ ሀገር ስልክ በማስደወል በመስሪያ ቤቱ ላይ 14 ሚሊዮን ብር ጉዳት መድረሱን የተመለከተ ሁለት ምርመራዎች ተጠናቀው በክስ ሂደት ላይ ሲሆኑ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች በሚፈጥሩት ጫና ክሱ እየተጓተተ ነው።
በትግራይ ክልል የሚገኘው በሼባ የብረታ ብረት ማቅለጫ ፋብሪካ ለፋብሪካው የተዘረጋው የኤሌክትሪክ ፍጆታ ቆጣሪ መሳሪያ ሥራውን በአግባቡ እንዳይሰራ በማድረግ መብራት ሀይል ከሽያጭ ማግኘት ይገባው የነበረውን ገቢ በማስቀረት በአገር ላይ 65 ሚሊዮን 300 ሺ ጉዳት በመድረሱ ምርመራው ተጣርቶ ለወሳኝ አካል ቢተላለፍም ውሳኔ ሳያገኝ ቀርቷል።
በተመሳሳይ በኦሮምያ ክልል በደብረዘይት የሚገኝ የግል የብረታ ብረት ማቅለጫ ፋብሪካ ለፋብሪካው የተዘረጋው የኤሌክትሪክ ፍጆታ ቆጣሪ መሳሪያ ሥራውን በአግባቡ እንዳይሰራ በማድረግ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ከሽያጭ ማግኘት ይገባው የነበረውን ገቢ በማስቀረት በአገር ላይ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት በማድረሱ ምርመራው አጣርቶ የፀረ ሙስና ኮሚሺን ቢልክም የፍትህ መጓተት ታይቶበታል።
በመብራት ሀይል አላግባብ በ 248 ሚሊዮን 900 ሺ ብር የተፈጸመ የ4 ሺ4 መቶ 70 ትራንስፎርመሮች አለም አቀፍ ግዢ በሁለት የምርመራ መዝገቦች የተጣራ ቢሆንም ውሳኔ አልተሰጠበትም።
ንብረቱ የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የብረት ማኑፋክቸሪንግ ማሽን ግንባታ ኢንዱስትሪ የሆነ ግምቱ 4 ሚሊዮን 7 መቶ ሺ የሆነ የብርና የነሃስ ሜዳልያ ከግምጃ ቤት በመጥፋቱ ተመርምሮ የተረጋገጠ ቢሆንም ውሳኔ አላገኘም።
በተንዳሆ ፕሮጀክት ከግብር ጋር በተያያዘ በመንግስት ላይ ጉዳት በመድረሱ ምርመራው ተጠናቆ ክስ ተመስርቷል። በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ በሊዝ እንዲስተናገድ የተወሰነለትን የመኖሪያ ቤት ኅ/ሥ/ማ ያለ ሊዝ በማስተናገድ የተሰጠ 30 ሺ 3 መቶ 32 ካ/ሜ ቦታ ምርመራ ተጠናቆ ክስ የተመሰረተ ቢሆንም ውሳኔ አላገኘም።
ለብሄራዊ ባንክ በሽያጭ ከሚቀርብ ወርቅ ጋር በተያያዘ የባንኩ ሰራተኞችና ነጋዴዎች በመመሳጠር 63 ሚሊዮን ብር በመመዝበር አስቀድሞ ተከሰው የነበሩ አሁን ጥፋተኛ ተብለው ጉዳዩ ለቅጣት ውሳኔ ተቀጥሯል።
በቂርቆስ ክ/ከተማ በልማት ተነሺዎች ስም ከመመሪያ ውጪ ግምቱ 13 ሚሊዮን 3 መቶ ሺ የሆነ 2, ሺ 1 መቶ 45 ካ/ሜትር ትርፍ መሬት አላግባብ በተሰጣቸው እና ከካሳ ክፍያም ጋር በተያያዘ 5 ሚሊዮን 2 መቶ ሺ ብር በትርፍ የተከፈላቸው ግለሰቦች ጉዳይ፤ በኢትዮጵያ የመድሃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ ሀዋሳ ቅርንጫፍ በእምነት ማጉደል ወንጀል ግምቱ ብር 1 ሚሊዮን 7 መቶ ሺ የሆነ መድሃኒት ተመዝብሮ ለግል ጥቅም መዋሉ እና በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በተደረገ የ100 ሚሊዮን የእህል ግዢ ጨረታ ግለሰቦች ሀሰተኛ ሰነድ በማቅረብ ጨረታውን ያሸነፉ መሆኑ በተደረገው ምርመራ በመረጋገጡ ጨረታው እንዲሰረዝና በግለሰቦቹ ላይ ክስ እንዲመሰረት የተደረገባቸው በጥቅሉ ከህዝብ በግብር የተሰበሰበ በርካታ ገንዘብ በአንድም በሌላ መልኩ በከፍተኛ አመራሮች ተጽእኖ በ2004 እና በ2005 ዓ.ም ተጣርቶ ለፍርድ ሰጭው አካል ቢተላለፍም ውሳኔ ሳይሰጥባቸው ቀርተዋል፡፡
ከ 7 መቶ ሚሊዮን ብር በላይ የመዘበሩ የስራ ሃፊዎች አልተቀጡም ሲል ከፀረ ሙስና ኮሚሺን የተገኘው መረጃ አመልክቷል፡፡ አሀዙ በ2005 የተፈጸመውን ሙስና አላካተተም።
ባለፉት 22 የኢህአዴግ የአገዛዝ አመታት የተፈጸሙና በጸረ ሙስና ኮሚሽን ያልተጣራ በሙስና የተዘረፈ ገንዘብ በቢሊዮኖች እንደሚቆጠር ይገመታል።

2013 Sakharov Prize for Freedom of Thought – seven nominations

2013 Sakharov Prize for Freedom of Thought – seven nominations

pizap_com10_89121895469725131379474868932
sep16-09-2013
The 2013 Sakharov Prize nominees, presented at a joint meeting of the Foreign Affairs and Development committees and the Human Rights Subcommittee on Monday, are: Malala Yousafzai (Pakistan), Edward Snowden (USA), Reeyot Alemu and Eskinder Nega (Ethiopia), Ales Bialatski, Eduard Lobau and Mykola Statkevich (Belarus), Mikhail Khodorkovsky (Russia), the “Standing Man” protesters (Turkey), and the CNN Freedom Project: Ending Modern – Day Slavery (USA).
Malala Yousafzai – nominated jointly by 3 political groups:
• for the EPP group, by José Ignacio Salafranca (ES), Elmar Brok (AT), Michael Gahler (DE), Arnaud Danjean (FR), Joseph Daul (FR), Gay Mitchell (IE) and Mairead Mc Guinness (IE),
• for the S&D group, by Hannes Swoboda (DE) and Véronique de Keyser (BE),
• for the ALDE Group, by Guy Verhofstadt (BE), Sir Graham Watson (UK), and Annemie Neyts-Uyttebroeck (BE),
and also by Jean Lambert (Greens, UK) and the ECR group.
Ms Yousafzai was 11 years old when she began her fight for the right to female education, freedom and self-determination in Pakistan’s Swat Valley, where the Taliban regime bans girls from attending school, by writing a blog under a pseudonym in 2009. She quickly became a prominent voice against such abuses, and Taliban gunmen tried to assassinate here in October 2012. She has since become symbol of the fight for women’s rights and worldwide access to education.
Edward Snowden – nominated by the Greens/EFA group and GUE/NGL group
A computer expert who worked as a contractor for the US National Security Agency and leaked details of its mass surveillance programmes to the press, Mr Snowden has been charged with espionage in the USA and is now living in temporary asylum in Russia.
Reeyot Alemu and Eskinder Nega – nominated by Ana Maria Gomes (S&D, PT) and 40 other MEPs
These Ethiopian journalists are serving prison terms on terrorism charges. Ms Alemu was sentenced in January 2012 after writing columns critical of the government, and Mr Nega was sentenced six months later, after criticizing the prosecution of journalists and dissidents in Ethiopia and writing about how an Arab Spring-like democracy movement might arise there.
Ales Bialatski, Eduard Lobau and Mykola Statkevich, representing all Belarusian political prisoners – nominated by Marek Migalski (ECR, PL), Filip Kaczmarek (EPP, PL), Jacek Protasiewicz (EPP, PL) and 39 other MEPs.
Belarusian presidential candidate Mr Statkevitch, “Malady Front” activist Mr Lobau, President of the “Viasna” Human Rights Centre Mr Bialiatski and other protesters have been in prison since December 2010, when they protested in the streets of Minsk about the “fraudulent” presidential elections that confirmed President Alexander Lukashenko in office.
Mikhail Khodorkovsky – nominated by Werner Schulz (Greens/EFA, DE) and 40 other MEPs
Russian businessman Mr Khodorkovsky was arrested on 25 October 2003, after calling on President Putin to account for systemic corruption and advocating an independent judicial system and respect for the rule of law. He was charged with fraud and sentenced in May 2005 to nine years in prison. In December 2010 further charges were brought against him, and his sentence was prolonged until 2017.
“Standing Man” protesters – nominated by Marietje Schaake (ALDE, NL) and 40 other MEPs
Erdem Gündüz was the first man to stand and stare in the Taksim Square protests in Istanbul, which started on 17 June 2013. Later he was joined by others, making this form of protest a symbol of the peaceful movement for a liberal society respecting human rights and freedoms.
The CNN Freedom Project: Ending Modern-Day Slavery – nominated by Boris Zala (S&D, SK) and 40 other MEPs
This global media campaign against the slave trade, human trafficking, and forced and child labour has issued over 400 reports since 2011 highlighting the suffering of victims from Mauritania to India to the Philippines.
Next steps
The Foreign Affairs and Development Committees and Human Rights Subcommittee will hold another joint meeting on 30 September to vote on the short list of the three finalists. The laureate will be chosen by Parliament’s Conference of Presidents on 10 October in Strasbourg and invited to the award ceremony on 20 November, also in Strasbourg.
REF. : 20130916IPR20013
Updated: ( 17-09-2013 – 10:15