Tuesday, October 14, 2014

በሸኮ መዠንገር ታጣቂዎችና በፌደራል ፖሊሶች መካከል በተደረገው የተኩስ ልውውጥ ከ50 በላይ የፌደራልና የመከላከያ አባላት ተገደሉ።


esat
ጥቅምት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት ባለፈው ቅዳሜና እሁድ የፌደራል ፖሊሶችን ልዩ ሃይልንና መከላከያን ባቀፈው የመንግስት ጦርና፣ መሳሪያ በታጠቁ የብሄረሰቡ ተወላጆች መካከል በተደረገው ውጊያ ከ40 በላይ የፌደራል ፖሊስ አባላትና
ከ10 ያላነሱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት፣ 4 ታጣቂ ሚሊሺያዎችና 3 የወረዳ ፖሊሶች ተገድለዋል። የሟቾቹ አስከሬን በሚዛን አማን ሆስፒታል እንዲገባ ከተደረገ በሁዋላ፣ ዘመድ ያላቸው ወደ ዘመዶቻቸው ሲሸኙ፣ የቀሪዎቹ የቀብር ስነስርዓት ደግሞ ሚዛን ውስጥ መፈጸሙን ለማወቅ ተችሎአል።
በአዲስ አበባ የፖሊስ ሆስፒታል ምንጮች እንደገለጹት ከሆነ ደግሞ በርካታ አስከሬን ወደ ሆስፒታሉ የገባ ሲሆን፣ በመዠንገሮች የተገደሉት የፌደራል ፖሊስ አባላት እጅግ ከፍተኛ መሆኑን የሚያመለክት ነው።
በሸኮና መዠንገር ታጣቂዎች በኩል የደረሰውን ጉዳት ለማወቅ ባይቻልም፣ በዛሬው እለት መንግስት ተጨማሪ ሃይል ወደ አካባቢው በመላክ ጥቃት መፈጸሙንና ብዙዎችን መግደሉን የአይን እማኞች ገልጸዋል።
ከብሄረሰቡ ውጭ ያሉ ሰፋሪ ነዋሪዎች በሚደርስባቸው ጥቃት የተነሳ ቀያቸውን እየለቀቁ ሲሆን፣ ብዙዎቹም ለከፋ ችግር ተዳርገዋል።
በፌደራል ፖሊሶች ላይ የደረሰውን ጉዳት በሚዛን አማን ሆስፒታልተገኝቶ የተመለከተ አንድ ወጣት፣ ሁኔታው አስከፊና አስፈሪ መሆኑን ገልጿል
በሌላ በኩል በአካባቢው ያለው የኢሳት ወኪል እንደገለጸው 18 የፌደራል ፖሊስ አስከሬን መቁጠሩን ተናግሯል። መንግስት ታንኮችንና ከባድ መሳሪያዎችን ማጓጓዙን ገልጾ፣ የሸኮ መዠንገር ተወላጆች ሚዛን ከተማ ድረስ በመምጣት ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ የሚያሳስብ
ወረቀት መበተናቸውንም ተናግሯል።በርካታ ቁጥር ያላቸው የተፈናቀሉ ኢትዮጵያን በሚዛን ከተማ ጎዳናዎች ላይ እንደሚታዩና እስካሁን እርዳታ ያደረገላቸው ድርጅት አለመኖሩንም ገልጿል።
መንግስት በጉዳዩ ላይ እስካሁን የሰጠው አስተያየት የለም። ከዚህ ቀደም በቴፒና ሜጤ በሚባሉት አካባቢዎች የነበረው ግጭት ወደ ጉራፈርዳ ወረዳ መሸጋገሩን እና የፌደራል ፖሊስ ወደ አካባቢው መሰማራቱን መዘገባችን ይታወሳል።
መስከረም አንድ በነበረው ግጭት መንግስት ከ 13 ያላነሱ ዜጎች መገደላቸውን ሲገልጽ፣ የአይን እማኞች የተገደሉትን ዜጎች ቁጥር ከ50 በላይ ያደርሱታል።

በቅርቡ የተሰደደው ጋዜጠኛ ሚሊዮን ሹሩቤ ህይወቱ አለፈ


Oct 14,2014
የማራኪ መፅሔት ባለቤት እና ማኔጂንግ ዳይሬክተር የነበረው ጋዜጠኛ ሚሊዮን ሹሩቤ በስደት በሚገኝበት ናይሮቢ ኬኒያ ዛሬ ጥቅምት 3 ቀን 2007 ዓ.ም. በድንገት ህይወቱ አልፏል፡፡ ኢህአዴግ መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት በጅምላ ያደረገውን የመፅሔቶች እና ጋዜጣ ክስ እና የበርካታ ጋዜጠኞችን እና ብሎገሮችን እስርን ፍርሃት ተከትሎ በቅርቡ ከተሰደዱ ጋዜጠኞች መካከል ጋዜጠኛ ሚሊዮን ሹሩቤ አንዱ ነበር፡፡
ሚልዮን ሹርቤ
ጋዜጠኛው በስደት ኬኒያ ከሚገኝበት አንድ ናይሮቢ ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቢቆይም ህይወቱን ማትረፍ እንዳልተቻለ ታውቋል፡፡ ጋዜጠኛው ከኢትዮጵያ ከተሰደደ ገና ሁለት ወር እንኳ እንዳልሞላው ለማወቅ ተችሏል፡፡ ጋዜጠኛው የድርሰት ስራም እንዳለው ተጠቁሟል፡፡ አዲስ ሚዲያም ለጋዜጠኛ ሚሊዮን ፈጣሪ ነፍሱን በገነት እንዲያኖር፤ ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹና አድናቂዎቹ መፅናናትን ይመኛል፡፡
maraki-magazine
ምንጭ፡ አዲስ ሚድያ

ከወያኔ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሾልኮ የወጣ

mof
ይህ ባለ 16 ገጽ ዘገባና ሰነድ ሲሆን ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ::

Sunday, October 5, 2014

ቅድመ ምርጫ 2007 እና የተቃውሚዎች እጣ ፋንታ (ሀይለሚካሄል ክፍሌ ከኖርዌይ ኦስሎ)

Election2007
ሀይለሚካሄል
መቼም የምርጫ ነገር ሲነሳ በኢትዮጵያ ታሪክ የጎላ ቀለም ያለው ምርጫ 97 ነው ምክንያቱም ከዚ በፊት የነበሩት ምርጫዎች በኢህአዲግም ሆነ በደርግ መንግስት የነበሩት የይስመላ ምርጫዎች ነበሩ ምርጫ 97ም ቢሆን የዲሞክራሲ ጭላንጭል የታየበት በአዲስ አበባ እስከ ምርጫው እለት ሲሆን በክልሎች ግን ምርጫው አንድ ወር እስኪቀረው ነበር በክልሎች ገዝው ኢህአዲግ ቀሪውን አንድ ወር አፈናውን እናወከባውን አጠናክሮ ከመቀጠሉም በላይ አልፎ አልፎ ጠንካራ ተፎካካሪዎች ባሉበት ክልል ግድያም ይፈፅም ነበር በአዲስ አበባም ቢሆን ከምርጫው ውጤት በዃላ የምርጫውን ውጤት በመቀልበስ የዲሞክራሲ ጭላንጭሉን አጨልሞታል ከዚያም በዃላ የምርጫውን ውጤት ተከትሎ በሃይል ገንፍሎ የወጣውን የህዝብ ቁጣ በሃይል ከመቀልበስ ውጭ አማራጭ ያጣው ኢህአዲግ አፈናውን እና ግድያውን አጠናክሮ በመላ ሃገሪቱ ቀጠለ እናም ተቀዋሚ ጎራው እጣ ፋንታውግማሹ እስር ቤት ግማሹም ኢህአዲግ ባሰመረለት መንገድ መሄድ ብቻ ሆነ እናም የምርጫ 97 ድራማ በዚህ መልኩ ተጠናቀቀ ቀሪው አምስት አመት ቀጣዩ ምርጫ እስኪመጣ ግምት ሰጥቶት የነበረውን የምክር ቤቱን ከ540አካባቢ መቀመጫ አንድ አራተኛ ለተቀዋሚ በመስጠት ያለውን የውጭ ጫና በማቅለል የተዘጉትን የእርዳታ ማእቀብ ለማስለቀቅ የሰራው የሂሳብ ስሌት ባለመሳካቱ እራሱን እንዲፈትሽ ምርጫው ትልቅ ማሳያ ሆኖታል በምርጫው ማግስት ኢህአዲግ ውጤቱን በሃይል መቀልበሱ በብዙዎች ቢታመንም ለኢህአዲግ ግን ውጤቱ ያልጠበቀው እና ያልተዘጋጀበት በመሆኑ በቀጣዩ የምርጫ ጊዜ ኢህአዲግ ካለፈው ተምሮ ብዙ ነገሮችን እንደሚያስተካክል የብዙዎች ግምት ቢሆንም ፓርቲው ግን ካለፈው ተምሬአለሁ የሚለውን የምፀት አባባል በአደባባይ እየተናገረ ለቀጣዩ 2002 የምርጫ ዘመን የሚከተለውን መዋቅር ዘረጋ
ከምርጫ 97 በዃላ በዋነኛነት የተወሰዱ እርምጃዎች 1 በህትመት እና በህትመት ውጤቶች ላይ ጫና መፍጠር እና አፋኝ የሆኑ የፕሬስ ህግ አዋጆችን መተግበር
2 በፀረ-ሽብር እንቅስቃሴ ከአሜሪካ ጋር በህብረት ፀረ-ሽብርተኝነትን መከላከል መርህ ሰበብ በምስራቅ አፍሪካ የአሜሪካ ዋነኛ አጋር በመሆን ጠቀም ያለ ወታደራዊ የቁስ እና የገንዘብ ድጋፍ ኢህአዲግ መራሹመንግስት እንደሚያገኝ ይታወቃል መንግስት ይሄንን የሽብር ጥቃት መከላከል በብ በመጠቀም በሃገርውስጥ የፀረ- ሽብር አዋጅ በማቋቋም ብሎም በመተግበር በሃገርውስጥ በሰላማዊ ትግል የተደራጁትን ፓርቲዎችን እና የነፃነት እና ዲሞክራሲ እጦት ተቋውሞ እንቅስቃሴዎችን በሽብርተኝነት በመፈረጅ አዋጁን በመጠቀም ብዙዎችን ለእስር በመዳረግ የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴዎችን መድረክ ማጥበብ ማቀጨጭ እና ብሎም ማጥፋት
3 በምርጫ 97 ከታዩት ጉልህ የኢህአዲግ ስህተቶች ወጣቱን በተለይ ሰራአጥ ወጣቶችን በአደገኛ ቦዘኔነት መፈረጅ እንዲሁም የተማረውን ሃይል ማግለል ስለነበር ይህንን እንደፓርቲው ስህተት በመቁጠር የሙሁሩን ጎራ በከፊልም ቢሆን መተካካት በሚል መርህ ጥቂት ጥቅማጥቅሞችን በማጋራት ብሎም ሙያዊ ሹመቶችን በመስጠት ልማታዊ ሙህር ልማታዊ ጋዜጠኛ ልማታዊ ዶክተር ወ.ዘ.ተ እያለ ወደዱም ጠሉም የፓርቲው አባል ማድረግ
4 ስራ አጥ ወጣቶችን በየቀበሌው እንዲደራጁ በማድረግ ባቋቋማቸው የማታለያ ገንዘብ ብድር ተቋማት ብድር በመፍቀድ እንዲደራጁ በመፍቀድ ሲደረግ ለዚህም የመጀመራያው መስፈርት የድርጅቱ አባል መሆን ሲሆን ለዚህም ዋናው አላማ ለተቀዋሚው ጎራ አባል ለመሆን እየሄደ የለውን ወጣት በጥቅማጥቅም ማስቀረት
5 ቀሪውን የህብረተሰብ ክፍል በተለይ ቀበሊ ነዋሪዎችን አንድ ለአምስት መርህ በኢህአዲግ ቋንቋ(መጠርነፍ)መያዝ እና በህዝቡ ቁጥር ልክ የሚመስል የደህንነት ሃይል ማሰማራት ይሄውም ተቀዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በህዝቡውስጥ ገብተው ምንም አይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ ማድረግ
6 ልማታዊ መንግስት በሚል መርህ በየመንደሩ በእርዳታ ድርጅቶች የተሰሩትን የውስጥ ለውስጥ መንገዶች በኮብል እስቶን በመቀየርለዚሁም በአብዛኛው ሰራ የሌላቸውን ወጣቶችን በማሰማራት አላማው ጥሩ ቢሆንም ከህብረተሰቡ የሚጠየቀው ገንዘብ ግን የተጋነነ ነው::
ኢህአዲግ ግን በዚህ ሲስተም በአንድድንጋይ ሁለት ወፍ የሚለውን የአባቶች አባባል ተጠቅሞበታል ይሄውም በልማት ሰበብ ለአባላቱ ጠቀም ያለ ገንዘብ ማስገኘት እና ሌላው አዳዲስ አባሎችን ማብዛትነው እንግዲህ እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትን የኢህአዲግ የ2002 የምርጫ ዝግጅት ማስቀየሻ ስልቶች ሲሆኑ እንደእቅዱ ሲተገበር ያተረፈው ነገር እጅግ ብዙ ቁጥር ያለው ደጋፊ ማፍራት ቢሆንም እውነታው ግን ኢህአዲግ ያፈራው እውነተኞቹን ደጋፊዎችን ሳይሆን በጥቅም የታሰሩትን እና ለሆዳቸው የተገዙ ደጋፊዎችን ሲሆን የዚህም የመጨረሻ ውጤት የደጋፊው ቁጥር በጨመረ ቁጥር የሁሉንም ጥቅም መጠበቅ አይቻልም ደጋፊዎችም ጥቅመኞች ስለሆኑ ልማታዊ ሳይሆኖ በተቃራኒው ሙሰኞች እና ዘራፊዎች ናቸው እናም የኢህአዲግ ጠላቶች የሚመነጩት ከራሱ ደጋፊዎች ሲሆን እነሱም እነዚህ በጥቅም የመጡቱ ጥቅማቸው በተቋረጠ ጊዜ የኢህአዲግ የመጨረሻ ጠላቶች ናቸው እንግዲህ ከላይ በጠቀስናቸው የማስቀየሻ ስልቶች ኢህአዲግ ምርጫ 2002ን ያለምንም ተቀናቃኝ ምርጫውን 99ፐርሰንት አሸንፌአለሁ ለማለት አስችሎታል ለዚሁም በአሸነፈ ማግስት የቀድሞው ጠ/ሚኒስት ሲናገሩ‹‹ ይህ ህዝብ ኢህአዲግ ካለፈው ስህተቱ የሚማር ፓርቲ መሆኑን ተገንዝቦ ለ5አመት ኮንትራቱን ሰጥቶናል ይህ ለኛ ትልቅ ማስጠንቀቂያ ነው ቃላችንን ካልጠበቅን በድምፁ የሰጠንን ካርድ መልሶ ይነጥቀናል›› ሲሉ አቶ መለስ የንቀት ንግግር አድርገዋል በአንፃሩ ግን እንዴት እንዳሸነፉ እራሳቸውም ህዝቡም ያውቃል እናም የ2002 ምርጫ እንከን የለሽ ምርጫ በሚል ድራማ ተጠናቋል በቀጣዩ መጣጥፍ በምርጫ 2007 ዘገባ ላይ ያተኮረ የዚህን መጣጥፍ ክፍል ሁለት ይዤ እቀርባለው እስከዚያው ቸር ይግጠመን