Saturday, August 17, 2013

የሥላሴዎች እርግማን (ሦስት) ፦ አዳክሞ ማደህየት

መስፍን ወልደ ማርያም
ሐምሌ 2005
አንድ በጣም የተገረመ ደቡብ አፍሪካዊ ይህንን ሁሉ መንገድና ሕንጻ በአንድ ጊዜ ለማሠራት ገንዘቡን ከየት ነው የምታገኙት? ብሎ ጠየቀኝና ከወርቅ-ቡና አልሁት፤ ሳቅ አለና እኔኮ ከልቤ ነው የምጠይቅህ አለኝ፤ እንግዲያው ዘክዝኬ ልንገርህ አልሁት፤ ለወትሮው ብዙ የምክር ዋጋ የሚያስከፍል ቢሆንም ለመንግሥትህ እንዳትናገርና የዚሁ ዓይነት ሥራ በደቡብ አፍሪካ እንዳይጀመር ቃል ግባልኝ አልሁትና ቀጠልሁ፤ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በመንግሥት ባንኮች ደጃፍ ላይ የነበረውን መጨናነቅ አይተሃል ወይ? ብዬ ጠይቄው ማየቱን ካረጋገጥሁ በኋላ ጉዳዩን እንደሚከተለው አስረዳሁት፡፡
አገዛዙ መሬቱንም ሆነ ቤቶችን የራሱ ካደረገና ባለቤትነቱን ካረጋገጠ በኋላ በየመንገዱ ዳር እንጀራ፣ ዳቦ፣ ቆሎ፣ ጠላና ትናንሽ ነገር እየሸጡ ልጆቻቸውን የሚያሳድጉ ሴቶች፣ በየቤቱ እየሠሩ በነዚህ ቤቶች ተዳብለው ኪራይ እየከፈሉ የሚኖሩ ሴቶች በብዛት ነበሩ፤ በነዚህ ደሀዎች ላይ ቀበሌዎች በየጊዜው እየዘመቱ ቤቱ እንደሚፈርስባቸው እያስፈራሩ ደሀዎችን ያሸብራሉ፤ በዚህ ዓይነት ፍርሃትና ስጋት ውስጥ ለጥቂት ወራት ካቆዩአቸው በኋላ ክረምትን ጠብቀው በግድ ያስለቅቁአቸዋል፤ በዚህ ምክንያት በአዲስ አበባ ውስጥ የተፈናቃይ ቁጥር በየዓመቱ እየጨመረ በአንዲት ትንሽ ክፍል ውስጥ የሚኖረው ሰው ቁጥር እየበዛ ለጤንነት ክፉ ጠንቅ እየሆነ ነው፤ ይህ ችግርና ስቃይ ትልቅ የሀብት ምንጭ ሆኖአል፤ ደሀ የሚበላው አንጂ የሚከፍለው አያጣም፤ ነጭ ደሀ ነጭ ማር ይከፍላል፤ እነዚህ ባህላዊ አነጋገሮች ተጠንተው በተግባር ላይ እየዋሉ ነው።
እንዴት? ማለት ጥሩ ነው፤ እነዚህ (ቤቶቻቸው ከማለት ይልቅ) መጠለያዎቻቸው የፈረሱባቸው ሰዎች ከረሀቡ ሌላ በብርድና በጸሐይ በመጉላላታቸው የመጠለያ ችግራቸው በጣም ከባድ ስለሆነ በቀላሉ የሚበዘበዙ ናቸው፤ ችግሩን መፍቻ የሚመስል የደሀውን ነፍስ በጉጉት ሰንገው የሚይዙበት ኮንዶሚንየም የሚባል ማቁለጭለጫም አለ፤ ደሀ ሁሉ ኮንዶ አግኝቶ የሚያልፍለት ይመስለዋል፤ ስለዚህ ሁሉም ይፈልጋል፤ ስለዚህ የኮንዶ ፈላጊው ሰልፍ በጣም ረጅም ነው፤ ስለዚህ በመስገብገብ እየተተኮሰ ዋጋው በጣም ከፍ ያለ ነው።
ማፍረስ ከመገንባት የቀለለ ቢሆንም በአዲስ አበባ የሚካሄደው አብዛኛው የመገንባት ሥራም ከማፍረሱ ሥራ የተሻለ መሆኑ በጣም ያጠራጥራል፤ እንዲያውም የማፍረሱንም ሆነ የመገንባቱን ሥራ የሚመሩት የውጭ አገር (ምናልባትም የቻይና) ሰዎች ናቸው ለማለት ያስደፍራል፤ በኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ነፍስ ውስጥ መሬት እንዳለ፣ በኢትዮጵያ የብዙ ሺህ ዓመታት ውስጥ መሬት እንዳለ፣ በኢትዮጵያ የተጋድሎ ጀግንነት ውስጥ መሬት እንዳለ፣ በኢትዮጵያ የአገር ፍቅር ውስጥ መሬት እንዳለ የውጩ አገር ሰው በምን መንገድ ሊያውቅ ይችላል? አንድ ኢትዮጵያዊ በአገሩ ውስጥ ባለው ቤት ውስጥ ምን ምን ይሠራል? አንዴት ይሠራል? በዚህ ጉዳይ ላይ የውጭ አገሩ ሰው ምንም ያህል አያውቅም፤
ስቱድዮ በወር አንድ መቶ ዘጠና አምስት ብር፣ ባለአንድ መኝታ ሁለት መቶ ሰባ አራት ብር፣ ባለሁለት መኝታ አምስት መቶ ብር እንደሚከፈል ተወስኖአል፤ ይህ ኪራይ ሁላችንም እንደምናውቀውና እንደለመድነው ዓይነት ያለ ኪራይ አይደለም፤ ልዩ ነው፤ አንዱ ልዩ የሚያደርገውም መጠለያዎቹን ሁሉ ያፈረሱትና ችግሩን የፈጠሩት ራሳቸው ኪራይ ሰብሳቢዎች መሆናቸው ነው፤ ዋናው ልዩ የሚያደርገው ግን ለኮንዶዎቹ ኪራይ መክፈል የሚጀመረው ሕንጻዎቹ ተሠርተውና አልቀው ተከራዮቹ ከገቡ በኋላ አይደለም፤ የሕንጻዎቹ ሥራ የሚጠናቀቀው ቢያነስ ከአምስት ዓመት በኋላ ሲሆን ኪራይ መክፈል የሚጀመረው ዛሬ ነው! ደሀዎች ለማይኖሩበት ቤት ኪራይ ይከፍላሉ! ማንም አላስገደዳቸውም፤ ያስገደዳቸው ደካማነታቸውና መናጢ ደሀነታቸው ነው፤ መስገብገባቸው ነው።
ከቀረበው መረጃ ተነሥተን እስቲ ትንሽ ስሌት እንሥራ፤ በአጠቃላይ በአዲስ አበባ ውስጥ ስምንት መቶ ሺህ ያህል ሰዎች ለኮንዶ ተመዝግበዋል እንበል፤ በስቱድዮ፣ በአንድ መኝታ፣ በሁለት መኝታ፣ በሦስት መኝታ በእያንዳንዳቸው የቤት ደረጃዎች ሁለት መቶ ሺህ ሰዎች ቢመዘገቡ     ከነዚህ ውስጥ ግማሽ የሚሆኑት በዝቅተኛ የደሀነት ደረጃ ላይ ቢሆኑ፣ ሢሶ የሚሆኑት ደግሞ የደሀነት መሀከለኛ ደረጃ ላይ ቢሆኑ፣ ሌሎቹ ማለትም አንድ አምስተኛ የሚሆኑት በተሻለ ደረጃ ላይ ያሉ ደሀዎች ቢሆኑ ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በያመቱ የሚሰበሰበው ገንዘብ እንደሚከተለው ይሆናል፤

ደሀነት ሲበዘበዝ
ኮንዶየተመዘገቡ  የወር ኪራይ በደሀነት ደረጃየዓመት ኪራይ
ስቱድዮ
200 000
 200 000 x 195=  39 000 000
  468 000 000
1 መኝታ
200 000
200 000 x 274=  54 800 000
  657 600 000
2 መኝታ
200 000
200 000 x 500= 100 000 000
1 200 000 000
3 መኝታ
200 000
200 000 x 750= 150 000 000
1 800 000 000
ድምር1 000 000               279 700 0004 125 000 000

እንግዲህ በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ ከመጠለያ ማጣት ጭንቀት ለማምለጥና ያደረባቸውን የኮንዶ ጉጉት ለማሳካት ከአራት ቢልዮን ብር በላይ እየተራቡ ይገብራሉ፤ በአምስት ዓመታት ውስጥ ገና ኮንዶው ውስጥ ሳይገቡ ላባቸውን ያንጠፈጠፉበትን 20 625 000 000 ብር ይከፍላሉ ግፍ ሌላ ትርጉም የለውም።
ማፍረስም በጣም ትርፋማ ሥራ ሆነ።
በፈረሰው ላይ የሚገነባውስ? ስለኮንዶው ሕንጻ አንዳንድ ጥያቄዎችን ማንሣት በግድ ያስፈልጋል፤ አንደኛ የኮንዶው ሥራ መቼ ተጀምሮ መቼ ያልቃል? ያልቃል ሲባልስ ለመኖሪያ ብቁ የሆነ፣ በሮችና መስኮቶች ተገጥመውለት፣ ወለሉና ጣራው፣ የመታጠቢያ ቤቱ ሁሉ ተሟልቶ ነው ወይስ ባለቤት የሚሆኑት ሰዎች የሚጠብቃቸው ሥራ አለው? ሁለተኛ የኮንዶው ሕንጻ ስንት ክረምትና ስንት በጋ የሚችል ይሆናል? ሦስተኛ ኮንዶው ሰዎችን ወደከፍተኛው ፎቅ የሚያደርሳቸው ‹ሊፍት› አለ ወይስ ሰዎች በእግራቸው በደረጃ ሊወጡ ነው? ይህ ከሆነ ለሽማግሌዎችና አሮጊቶች ምን ዝግጅት ተደርጎላቸዋል? ሽማግሌዎችንና አሮጊቶችን ወደምድር ቤቱ አካባቢ ለመደልደል ታስቦአል ወይ? አራተኛ የውሀ አቅርቦቱ ምን ያህል አስተማማኝ ነው? ውሀ በሚጠፋበት ጊዜ ነዋሪዎቹ ሊጠቀሙበት የሚችሉበት የመጸዳጃ ቦታ ካልተዘጋጀ በጥቂት ጊዜ ውስጥ አካባቢው ለጤና ጠንቅ እንደሚሆን መገመት አያዳግትም፤ ‹‹የአበሻ ኑሮ›› የሚባል ነገር ያለ ይመስለኛል፤ ቡናና ጌሾ መውቀጡ፣ ብቅልና በርበሬ ማስጣቱ፣ ዶሮና በግ ማረዱ፣ አንጀራ መጋገሩ፣ ማኅበሩ፣ ለቅሶው — እነዚህና ሌሎችም ማኅበራዊ ግዴታዎች ኮንዶው ሲሠራ ታስበው ነበር ወይ?
ደሀው ራሱን በማፈራረስ፣ ይበልጡኑ በሚደኸይበት ሥራ እንዲጠመድ፣ በፍርስራሽ እንዲነግድ በምናምን ተይዞአል! የሥላሴዎች እርግማን!

Police Foil Plan to Attack Addis Ababa Airport

Ethiopia: Police Foil Plan to Attack Addis Ababa Airport


Note: Do not forget reading Wikileaks’ files below ”Recent Bombings Blamed on Oromos Possibly the Work of Government of Ethiopia” and “Ethiopia Bombs Itself, Blames Eritrea
Aug 17, 2013, Addis Ababa (All africa)— The Ethiopian federal police said on Friday that they have uncovered explosive devices planted inside, Addis Ababa Bole International Airport, averting a major tragedy.
Two explosives were found around the departure terminal of the country’s largest airport targeting the hundreds of passengers waiting to fly.
The incident created panic among passengers and caused a delay in flights until bomb disposal experts were able to dismantle the devices, which are believed to have been home made, and cleared the rest of the area for other explosive devices.
It is not clear how the attackers managed to pass the number of security check points at the airport.
A police official told Sudan Tribune that the nature of the attack is under investigation and it is yet to be determined if the attempt was a terrorist attack.
“It is safe now and no more threats. There is nothing to worry” about the source, who requested anonymity, said.
Airport authorities have placed the international airport on high alert with a heavy security presence.
Addis Ababa Bole International Airport is among Africa’s three busiest hubs.
–All Africa

Wikileaks Ethiopia Files: Ethiopia Bombs Itself, Blames Eritrea

by Thomas C. Mountain
Foreign Policy Journal | September 16, 2011
secreexpot
Recently released Wikileaks Ethiopia files expose how Ethiopian security forces planted 3 bombs that went off in the Ethiopian capital Addis Ababa on September 16, 2006 and then blamed Eritrea and the Oromo resistance for the blasts in a case that raises serious questions about the claims made about the bombing attempt against the African Union summit earlier this year in Addis Ababa, Ethiopia.
In a report  from 2006 marked “Secret ; Subject: Ethiopia: Recent Bombings Blamed on Oromos Possibly the Work of GOE [Government of Ethiopia]” “Classified By: Charge [d’Affairs] Vicki Huddleston”, “An embassy source, as well as clandestine reporting, suggests that the bombing may have in fact been the work of the GoE security forces.” (Cable reference id: #06ADDISABABA2708.)
At the time, the western media reported the Ethiopian National Intelligence and Security Service (NISS) claims that the bombs were “part of a coordinated terror attack by the OLF [Oromo Liberation Front, the oldest national  liberation movement in Ethiopia] and  Sha’abiya (Eritrea) aimed at disrupting democratic development”.
The Wikileaks report goes on, “a typically reliable information source” who “contacted Post to report that” the bodies of three men found at the bomb sites “had been picked up by police a week prior, kept in detention and tortured. He said police then left the men in a house and detonated explosives nearby, killing 3 of them.”
This exposes the history of how the Ethiopian regime has planted bombs and then blamed Eritrea and the Ethiopian resistance. The lies that make up the official version of this alleged terrorist attack raises serious questions about the credibility of the recently released report by the UN via its US State Department affiliate, the Monitoring Group for Eritrea and Somalia, which blames the Eritreans and the OLF for the January bombing attempt at the African Union summit in Addis Ababa, Ethiopia. Identical lies about a nearly identical “terrorist attack”, all accepted as fact by the western media. This should also deliver another body blow to the Obama White House and its claims that Eritrea supports terrorism in the Horn of Africa.
So once again the bellowing against Eritrea by the USA and it lackeys at the UN going back to 2006 is exposed as complete bunkum and an identical frame up of Eritrean and the Oromo resistance in Ethiopia that has been regurgitated by the UN and its truth challenged Monitoring Group on Eritrea and Somalia must be subject to a more critical scrutiny. Based on this expose’ it can only be hoped that the UN inSecurity Council, which has yet to decide whether to pass severe sanctions against Eritrea, will refrain from doing so.
Foreign Policy Journal

SUBJECT: ETHIOPIA: RECENT BOMBINGS BLAMED ON OROMOS
POSSIBLY THE WORK OF GOE

Wikileaks
terrorwork
Classified By: CHARGE VICKI HUDDLESTON FOR REASONS 1.4(b)AND(d).
¶1. (S) SUMMARY A series of explosions were reported in Addis Ababa on September 16, killing three individuals. The GoE announced that the bombs went off while being assembled, and that the three dead were terrorists from the outlawed Oromo Liberation Front (OLF) with links to the Oromo National Congress (ONC). An embassy source, as well as clandestine reporting, suggests that the bombing may have in fact been the work of GoE security forces. END SUMMARY
¶2. (U) On September 16, three bomb explosions were reported in the Kara Kore area of Addis Ababa. The explosions were heard at 4:45 a.m., 7:00 a.m., and 10:00 a.m. The National Intelligence and Security Service (NISS), together with the Federal Police Anti-terror Task Force later reported that the bombs were “part of a coordinated terror attack by the OLF and Sha’abiya (Eritrea) aimed at disrupting democratic development.” The NISS said that the intended terror plot had failed and the bombs had mistakenly gone off while the suspects were preparing them while hiding out at an illegally built house. Two of the suspects died immediately, while another died on the way to the hospital. One other is in critical condition. The police task force reported having others in custody related to the plot and that evidence shows the terrorists had ties to Oromo groups – the Mecha and Tulema Association (MTA) and the ONC. They also said that the bombs used contained parts sourced from Eritrea and were consistent with bombs used in previous terrorist attacks.
¶3. (S) On September 20, Dr. Merera Gudina (strictly protect), the former leader of the ONC (and a typically reliable information source), contacted Post to report that the deceased had not died not while constructing a bomb, but rather at the hands of GoE cadres. Dr. Merera said that the men had been picked up by police a week prior, kept in detention and tortured. He said police then left the men in a house and detonated explosives nearby, killing 3 of them. He did not indicate whether the men were ONC or OLF affiliated.
¶4. (S) Clandestine reporting indicates that the bombs did not explode inside the structure, but rather appear to have been placed outside and detonated.
[Ambassador Vicki] HUDDLESTON

የኢህአዴግ የፖለቲካ ዥዋዥዌ

የኢህአዴግ የፖለቲካ ዥዋዥዌ

      የኢህአዴግ የፖለቲካ ዥዋዥዌ
እንቆቅልሽ እየሆነ የሚያስቸግረን የኢህአዴግ የፖለቲካ ዥዋዥዌ፤ በአብዛኛው ጊዜያዊ ጨዋታ ሳይሆን፤ ከራሱ ከኢህአዴግ ተፈጥሮ የሚመነጭ ነባር ባህርይ ነው። ኢህአዴግ በተፈጥሮው፤ “አንድም፤ ሁለትም ነው” ማለት ይቻላል። አንድም “አብዮታዊ” ልሁን ይላል፤ ሁለትም “ዲሞክራሲያዊ” ልሁን ይላል። አንደኛውንና ገናናውን “አብዮታዊ ኢህአዴግ”፤ ሌላኛውንና አናሳውን “ዲሞክራሲያዊ ኢህአዴግ” ብለን ልንሰይማቸው እንችላለን። ይህንን መንታ ማንነት፤ በሁሉም የኢህአዴግ አስተሳሰቦች ውስጥ ታገኙታላችሁ።

ለምሳሌ የኢኮኖሚ አስተሳሰቦቹን ተመልከቱ። አንድም፤ “ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል” እያለ የሚሰብክ ሶሻሊስት ነው። ሁለትም፤ “ያፀደቅኩት ህገመንግስት ነጭ ካፒታሊዝምን ያሰፍናል” እያለ የሚናገር ነው። በፓለቲካውስ? አንድም፤ “የቡድን መብት፤ የብሄር ብሄረሰብ መብት፤ የብዙሃን መብት” እያለ ህዝባዊነትን (ሶሻሊዝምን) ይደሰኩራል። ሁለትም፤ “የግለሰብ መብት የህገመንግስታዊ ስርአታችን አንድ ምሶሶ ነው” በማለት ይናገራል።
አንዳንዴ “ኢህአዴግ” ይነሳበታል፤ እናም ወደ ግራ አቅጣጫ ይንደረደራል። ሌላ ጊዜ ደግሞ፤ ሰከን ብሎ “ዲሞክራሲያዊው ኢህአዴግ” ይባንናል፤ ያኔ ወደ ቀኝ አቅጣጫ ይንፏቀቃል። በእርግጥ እንዲህ በተቃርኖ ተወጥሮ እስከ ወዲያኛው መዝለቅ አይችልም። ፈጠነም ዘገየም፤ ወደ አንዱ አቅጣጫ እያመዘነ መሄዱ የማይቀር ነው (በተቃርኖ ተወጥሮ መፍረስ ወይም መፈንዳት ካልፈለገ በቀር)። ከሁለቱ ተቃራኒ አቅጣጫዎች (ከሁለቱ ተቃራኒ ማንነቶች) መካከል አንዱ እስኪያሸንፍ ድረስ ግን፤ ተቃራኒዎቹ ማንነቶች እየተፈራረቁ በዥዋዥዌ አገሪቱን ይዞ በአዙሪት መሾሩ ይቀጥላል።
ኢህአዴግና ዲሞክራሲያዊው ኢህአዴግ፤ ምን ያህል ተቃራኒ አቋሞችን እንደሚይዙ ለማየት፤ የተለያዩ ርእሰ ጉዳዮችን በማንሳት እንመልከት። በቢዝነስና በመንግስት ጣልቃ ገብነት ላይ፤ በኪራይ ሰብሳቢና በጥገኛ፤ በተቃዋሚ ፓርቲና በሚዲያ ክርክር ላይ፤ በህገመንግስትና በአገራዊ መግባባት ላይ፤ “ሁለቱ ኢህአዴጎች” በአቋም ይለያያሉ። ሌላው ይቅርና በዲሞክራሲና በአብዮት ላይ ያላቸው አቋምም ለየቅል ነው። አንዳንዶቹን ለመመልከት እንሞክር።
“ኢህአዴግ”፤ የኛ ዲሞክራሲና የፖለቲካ ምርጫ ከአሜሪካ ይበልጣል ይላል - የመራጮች ተሳትፎ በኢትዮጵያ ከፍተኛ መሆኑን በመጥቀስ። በአሜሪካ፤ መምረጥ ከሚችለው ህዝብ መካከል ከ60 በመቶ በታች ያህሉ በምርጫ ይሳተፋል። በኢትዮጵያ ግን ከ85 በመቶ በላይ ድምፅ በመስጠት ይሳተፋል በማለት ያብራራል  ኢህአዴግ። ኮሙኒስቶች የሚያዘወትሩት አባባል መሆኑን ልብ በሉ። የአንድ ፓርቲ አገዛዝና፤ እንደ ሳዳም ሁሴን የመሳሰሉ አምባገነኖች በነገሱባቸው አገራት ውስጥ፤ ከ90 በመቶ በላይ ህዝብ በምርጫ ይሳተፍ እንደነበረ ግን አይወራም።

በአሜሪካ እንደሚታየው፤ በቀጥታ የሚተላለፍ የፓርቲዎችና የፖለቲከኞች ክርክር አስፈላጊ እንዳልሆነ የሚገልፀው “ኢህአዴግ”፤ በቀጥታ ስርጭት የህዝብ ጥያቄች ጎልተው አይወጡም በማለት ያጣጥለዋል። የፖርቲዎች ክርክር በሚዲያ ከመሰራጨቱ በፊት “ኤዲት” ሲደረግ፤ የህዝብ ጥያቄዎች ጎልተው ይወጣሉ በማለትም ይከራከራል።
“ኢህአዴግ” በበኩሉ፤ የአሜሪካ ዲሞክራሲ እጅግ የዳበረ እንደሆነና ኢትዮጵያም ቀስ በቀስ ዲሞክራሲን በመገንባት እንደምታዳብር ይገልፃል። በቀጥታ የሚሰራጭ የፓርቲዎችና የፖለቲከኞች ክርክር፤ በአሜሪካ እንደሚታየው ከጠንካራ የዲሞክራሲ ባህል ጋር የተሳሰረ እንደሆነና ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው በአድናቆት ይናገራል ኢህአዴግ”። በኢትዮጵያ ግን የዲሞክራሲ ባህል ስላልዳበረ፤ በቀጥታ የሚሰራጭ የፓርቲዎች ክርክር፤ እንደ 97ቱ ምርጫ ስሜታዊነትንና ግጭትን ይፈጥራል የሚለው  ኢህአዴግ”፤ ቀስ በቀስ ዲሞክራሲያዊ ባህል ማዳበር አለብን ይላል።
ከአንድናት ኢትዮጵያ ብሎግ


ኢትዮጵያ ክብር ለዘላለም ትኑር!

የኢህአዴግ ውድቀት አይቀሬነት ነው

የኢህአዴግ ውድቀት አይቀሬነት ነው

በሀገራችን ከቀን ወደ ቀን እያደጉና አየገዘፉየመጡትን የህዝብን የለውጥ ጥያቄዎችኢህአዴግ አጥጋቢ መልስ ሊሰጥ አልቻለም፡፡እነዚህ የለውጥ ጥያቄዎች መልስ ሊያገኙያልቻሉበት ዋንኛ ጉዳይ፣ የሀገሪቱ ተቋማትለህዝቡ ጥያቄ የሚመጥን መልስ መስጠትየማይችሉ በመሆናቸው ነው፡፡ በአጭሩየተቋማቱ ውድቀት እንደሆነ ያለምንም ብዥታእንረዳለን፡፡

በሃይማኖት ተቋማት ላይ ተነሱ የሕዝብጥያቄዎች ብንመለከት፡፡ ኢህአዴግ አገሪቱንከተቆጣጠረበት ጊዜ ጀምሮ እጁን በቀጥታበሃይማኖቶች ውስጥ ማስገባቱን እንረዳለን፡፡በነጋ በመሸ ቁጥር ብዙ የሚባልለትህገ-መንግስት “መንግስት በሃይማኖት፣ሃይማኖት በመንግስት ጉዳይ ጣልቃአይገባም” ቢልም፣ በተግባር ግን ሕዝብየሃይማኖት መሪዎቹና በመንግስት ካድሬዎችመካከል ያለውን ልዩነት መለየት የተቸገረበትወቅት ላይ ነው የደረሰው፡፡ የሙስሊሙህብረተሰብ ላለፉት ዓመታት ጠንካራየሃይማኖት ተቋም እንዲኖረው ያለማሰለስጠይቋል፡፡ 1997 .መደረግየነበረበትን የሃይማኖቱ መሪዎች ምርጫ እስካሁን ባለመደረጉ በተለያዩ አጋጣሚዎች ቅሬታውን ሲገልጽ ሰንብቷል፡፡ መጅሊሱከኢህአዴግ ተላላኪነት ራሱን አውጥቶ፣ ሕዝበ ሙስሊሙን እንዲመራ ያለመሰልቸት ጠይቋል፡፡ እነዚህን የሕዝበ ሙስሊሙጥያቄዎች፣ መጅሊሱ መፍትሄ ሊያበጅለት አልቻለም፡፡

ሲንከባለሉ የመጡ ችግሮች በእንዲህ እንዳሉ፣ መንግስት በግልጽ የአንድ ሃይማኖት አስተሳሰብ በሙስሊሙ ላይ ለመጫንተነሳ፡፡ ይህን አስተሳሰብ ለማስረፅ በተዘጋጁ ስልጠናዎች ላይ መንግስት በግልጽ የዚህ አስተሳሰብ ደጋፊነቱን ማወጁ፣ብዙዎችን አስደነገጠ፤ አስቆጣም፡፡ ዘወትር የሚምልበትን ሕገ-መንግስት በግላጭ ጣሰ፡፡ ሰልጣኞቹ በካድሬዎች እየተመለመሉሥልጠና እንዲወስዱ ዋንኛ ስራ አድርጐት ቀጠለ፡፡ ይህን ድርጊቱን የተቃወሙ ሙስሊሞችን “አክራሪዎች” የሚል ተለጣፊስም በመስጠት ልዩነቶችንና አለመግባባቶችን ይበልጥ እንዲሰፉ አደረገ፡፡ በዚህ መሃል መጅሊሲ የመፍትሄው አካል መሆንሲገባው፣ የችግሩ አካል ሆኖ በግልጽ ወጣ፡፡

የሙስሊሙን ህብረተሰብ መሠረታዊ የመብት ጥያቄዎች ኢህአዴግ አጥጋቢ በሆነ መልኩ ሊቀርፋቸው ሲገባ፤ የህዝበሙስሊሙን ወኪሎች እንደለመደው ለቁጥር የሚያዳግት ታፔላ ለጠፈባቸው፤ በህገ-ወጥነት፣ በተላላኪነት፣ በአሸባሪነት፣በሃይማኖት ጽንፈኛነት /አክራሪነት/ በፀረ-ሰላምና ፀረ-አንድነት፣ በሃይማኖት ሽፋን ፖለቲካ አጀንዳ የሚያራምዱ፣ የነውጥኃይል ወደሚል ፍረጃ ገባ፡፡ ሕዝበ ሙስሊሙ ግን እጅግ ጨዋነት በተሞላበት፣ ከስሜት በወጣና ብዙዎቻችን ባስደመመመልኩ፣ ፍጹም ሰላማዊ
የሆነ ተቃውሞውን ቀጠለ፡፡

በዚህ ሰላማዊ እንቅስቃሴ የተበሳጨው ኢህአዴግ፣ የጸጥታ ኃይሎችን ወታደሮችንእና ፌደራል ፖሊስን በማሰማራትሙሰሊሙ ላይ ያልተመጣጠነ የኃይል እርምጃ ወስዷል በዚህም ጥቂት የማይባሉ ወንድሞቻችን ና ወገኖችንን ገድሏልመስጂድ ሰብሮ በመግባት የተከበሩ የእምነት ተቋማትን ክብር ደፍሯል፡፡ በመጨረሽያም በህዝበ ሙሲሊሙ የተመረጡ የኮሚቴአባለትን  ጋዜጠኞችን በጅምላ አስሯል፡፡ በቅርቡ አምኒስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው ሪፖርት እንዳመለከተው በታሰሩትየሙስሊም ተወካዮች ላይ የሰባዓዊ መብት ጥሰት መፈጸሙን ዘግቧል በአፋጣኝ እንዲያቆምም ጠይቋል፡፡ በተለይ የሙስሊሙመሪዎች ላይ ድብደባና ቶርቸር መፈጸሙን ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡

የሃማኖት ተቋም ነጻነት ጥያቄ አንግበው የተነሱ ወገኖችን ላይ የደረሰውን የሰባዓዊ መብት ገፈፋን አጥብቀን እናወግዛለን፤ በዚህተግባር የተሳተፉ አካላትም የፈጸሙት የሰባዓዊ መብት ጥሰት በኃላፊነት እንደሚያስጠይቃቸው መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡

የህዝበ ሙስሊሙ የመብት ጥያቄ በዱላ፣ በጠመንጃና በእስር መፈፀሙ አይፈታም ብለን እናምናለን፡፡ የህዝበ ሙሰሊሙ ጥያቄሊፈታ የሚችለው የኔ የሚለው፣ ሊወክለው የሚችል፣ ከፖለቲካ ጣልቃ ገብነት የፀዳ ነጻና ጠንካራ ተቋም ሲመሰርት ብቻነው፡፡

በክርስትና የሃይማኖት ተቋማት (በተለይም በኦርቶዶክስ ተዋህዶውስጥ የሚታየው ጉድ፣ ከሙስሊሙ ተቋማ ከሚታየውችግር ከአስር እጥፍ በላይ የገዘፈ ነው የሚል እምነት አለን፡፡ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ታምራት ላይኔ ከእስር ከተፈቱ በኃላከአሜሪካ ኤምባሲ ኃላፊዎች ጋር ያደረጉትን ወይይት ዊኪሊክስ ይፋ ማድረጉ ይታወቃል፡፡ በዚህ ውይይት ላይ አቶ ታምራትእንደገለጹት “የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትሪያሪክ አቡነ መርቆሪዮስን በእኔ ፊርማ ከቦታቸዉ እንዲነሱ አድርጌ፣ ለእኛስርዓት ይሰሩልናል ያልነዉን እንዲሾሙ አድርገናል” ብለዋል፡፡

በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ውስጥ ተቋማዊ አሰራር ብሎ ነገር የለም፡፡ ሲኖዶሱ ትርጉም ያለው አካል መሆን አልቻለም፤ተሰብስቦ የሚወስነው ውሳኔ ተግባራዊ አይሆንም፡፡ በሲኖዶስ ስብሰባ ላይ የመንግሰት ከፍተኛ ባለስጣናት እየተገኙየሚፈልጉትን ውሳኔ እያስወሰኑ ወንጀል ሲፈጽሙ ቆይተዋል፡፡ “ለምን? እንዴት?” በማለት ጥያቄ ያቀረቡ ጳጳሳትመስቀላቸውን እያስቀመጡ ቤተመንግሥት እንዲገቡ ከተደረጉ በኋላ ዛቻና ማስፈራሪያ ተፈጽሞባቸዋል፤ በመኖሪያቸውውስጥም የተደበደቡ አባቶች አሉ፡፡

መንግሥት ካላጣው መሬት በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮች ታላቅ የቅድስና ቦታ ተደርጎ የሚቆጠረውን ዋልድባ ገዳምበእብሪትና በማን አለብኝነት በልማት ስም ደፍሯል፡፡ የዋልድባ ገዳም መጋቢና የገዳሙ ምሰሶ ሆነው በዙሪያው የሚገኙ ሶስትቤተክርስቲያናትን አፈራርሶል፡፡ በገዳሙ ውስጥ ለረጅም ዓመታት በምንኩስና የሚኖሩ አረጋዊያንና ገዳሙን የሚያገለግሉአትንኩብን፤ የእምነት ነፃነታችን ይከበር” ብለው ቢጮሁ “ፀረ-ልማት፤ ሽብርተኞችእያለ አሸማቋቸዋል፡፡

ኢህአዴግ ከአፈጣጠሩ ስናየው ሁሉን የመቆጣጠር አቅጣጫ የሚከተል ኃይል ነው፤ ቀጥተኛ የሆነውን የሙስሊሞችን የተቋምነጻነት ጥያቄ እንኳን መፍቀድ የማይፈልግ አምባገነን ነው፡፡ በመሠረቱ የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ፍልስፍና በኢኮኖሚ፣በፖለቲካም ሆነ በማህበራዊ ዘርፍ ከሱ ቁጥጥር ውጭ የሆነ ተቋማትን በሀገራችን እንዲያብቡ በፍፁም አይፈቅድም፡፡ ያለፉት21 ዓመታት ሂደቱ በግልጽ የሚያሳየው ይህንኑ ነው፡፡

ነጻ ተቋማት ሊኖሩ የሚችሉት ዴሞክራሲና ነጻነት በተከበረበት ሀገር ብቻ ነው፡፡ ስለሆነም ሁላችንም ለዴሞክራሲያዊ ስርዓትምስረታና ለሰባዓዊ መብቶች መከበር ለሚደረገ ትግል የድርሻችንን ልናበረክት ይገባል፡፡
ከአንድናት ኢትዮጵያ ብሎግ


ኢትዮጵያ ክብር ለዘላለም ትኑር!