Friday, January 2, 2015

አርማጮ በአማራ ንቅናቄ ሰራዊት እና በወያኔ ሰራዊት በውጊያ ተወጥራለች




  • 3779
     
    Share

(ምንሊክ ሳልሳዊ)
በአርማጮ አከባቢ በአማራ ንቅናቄ ሰራዊት እና በወያኔ ሰራዊት መካከል ከባድ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን የንቅናቄው ምንጮች ከአከባቢው አስታወቁ::የህዝቡ ተሳትፎ በከፍተኛ ደረጃ እየታየ ባለበት እና ህዝቡ እና የንቅናቄው ወታደሮች በመቀናጀት ዱር ቤቴ ብለው ወደ ጫካ መግባታቸው ሲታወቅ በመተማ ሸዲ አከባቢ በትላንትናው እለት በወያኔው ጦር ላይ ጥቃት አድርሶ ወደቦታው የተመለሰው የአማራ ንቅናቄ ሰራዊት ከሕዝቡ ጋር በመተባበር እጅግ በርካታ የጦር መሳሪያዎችን እንደማረከ ምንጮቹ ተናግረዋል::

(ፎቶ ከፋይል)
(ፎቶ ከፋይል)

ካለፈው አርብ ጀምሮ የተነሳው ውጊያ በአሁን ወቅት ቀጥሎ ያለ ሲሆን በዛሬው ለሊት ከፍተኛ የቶክስ እሩምታዎች እና የከባድ መሳሪያ ድምጾች በአከባቢው እየተሰሙ መሆኑ ታውቋል::በአብድራፊ አብሃጂራ ሶረቃ ግጨው ማርዘነብ ማይጸማር ሃሙስ ገበያ ዳንሻ ማይካድራ እና አከባቢው ጦርነቱ ይስፋፋባቸዋል የሚል ከፍተኛ ስጋት ስላደረ በአከባቢው የወያኔ ሰራዊቶች በብዛት መስፈራቸው ሲታወቅ አዳዲስ ታንኮችን የጫኑ ከባባድ መኪኖች በቦታው ደርሰዋል:: እንዲሁን ወደ ሱዳን ክልል ዘልቀው የገቡ እና ከሱዳን ወታደሮች ጋር አሰሳ የሚያደርጉ ወያኔዎችን እንዳጠቁ የአማራው ንቅናቄ ወታደሮች ተናግረዋል::
በአርማጮ እና አከባቢው የተከሰተውን ግጭት በተመለከተ የአማራ ንቅናቄ ሰራዊት መግለጫ ያወጣል ተብሎ ይጠበቃል::

Tuesday, October 14, 2014

በሸኮ መዠንገር ታጣቂዎችና በፌደራል ፖሊሶች መካከል በተደረገው የተኩስ ልውውጥ ከ50 በላይ የፌደራልና የመከላከያ አባላት ተገደሉ።


esat
ጥቅምት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት ባለፈው ቅዳሜና እሁድ የፌደራል ፖሊሶችን ልዩ ሃይልንና መከላከያን ባቀፈው የመንግስት ጦርና፣ መሳሪያ በታጠቁ የብሄረሰቡ ተወላጆች መካከል በተደረገው ውጊያ ከ40 በላይ የፌደራል ፖሊስ አባላትና
ከ10 ያላነሱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት፣ 4 ታጣቂ ሚሊሺያዎችና 3 የወረዳ ፖሊሶች ተገድለዋል። የሟቾቹ አስከሬን በሚዛን አማን ሆስፒታል እንዲገባ ከተደረገ በሁዋላ፣ ዘመድ ያላቸው ወደ ዘመዶቻቸው ሲሸኙ፣ የቀሪዎቹ የቀብር ስነስርዓት ደግሞ ሚዛን ውስጥ መፈጸሙን ለማወቅ ተችሎአል።
በአዲስ አበባ የፖሊስ ሆስፒታል ምንጮች እንደገለጹት ከሆነ ደግሞ በርካታ አስከሬን ወደ ሆስፒታሉ የገባ ሲሆን፣ በመዠንገሮች የተገደሉት የፌደራል ፖሊስ አባላት እጅግ ከፍተኛ መሆኑን የሚያመለክት ነው።
በሸኮና መዠንገር ታጣቂዎች በኩል የደረሰውን ጉዳት ለማወቅ ባይቻልም፣ በዛሬው እለት መንግስት ተጨማሪ ሃይል ወደ አካባቢው በመላክ ጥቃት መፈጸሙንና ብዙዎችን መግደሉን የአይን እማኞች ገልጸዋል።
ከብሄረሰቡ ውጭ ያሉ ሰፋሪ ነዋሪዎች በሚደርስባቸው ጥቃት የተነሳ ቀያቸውን እየለቀቁ ሲሆን፣ ብዙዎቹም ለከፋ ችግር ተዳርገዋል።
በፌደራል ፖሊሶች ላይ የደረሰውን ጉዳት በሚዛን አማን ሆስፒታልተገኝቶ የተመለከተ አንድ ወጣት፣ ሁኔታው አስከፊና አስፈሪ መሆኑን ገልጿል
በሌላ በኩል በአካባቢው ያለው የኢሳት ወኪል እንደገለጸው 18 የፌደራል ፖሊስ አስከሬን መቁጠሩን ተናግሯል። መንግስት ታንኮችንና ከባድ መሳሪያዎችን ማጓጓዙን ገልጾ፣ የሸኮ መዠንገር ተወላጆች ሚዛን ከተማ ድረስ በመምጣት ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ የሚያሳስብ
ወረቀት መበተናቸውንም ተናግሯል።በርካታ ቁጥር ያላቸው የተፈናቀሉ ኢትዮጵያን በሚዛን ከተማ ጎዳናዎች ላይ እንደሚታዩና እስካሁን እርዳታ ያደረገላቸው ድርጅት አለመኖሩንም ገልጿል።
መንግስት በጉዳዩ ላይ እስካሁን የሰጠው አስተያየት የለም። ከዚህ ቀደም በቴፒና ሜጤ በሚባሉት አካባቢዎች የነበረው ግጭት ወደ ጉራፈርዳ ወረዳ መሸጋገሩን እና የፌደራል ፖሊስ ወደ አካባቢው መሰማራቱን መዘገባችን ይታወሳል።
መስከረም አንድ በነበረው ግጭት መንግስት ከ 13 ያላነሱ ዜጎች መገደላቸውን ሲገልጽ፣ የአይን እማኞች የተገደሉትን ዜጎች ቁጥር ከ50 በላይ ያደርሱታል።

በቅርቡ የተሰደደው ጋዜጠኛ ሚሊዮን ሹሩቤ ህይወቱ አለፈ


Oct 14,2014
የማራኪ መፅሔት ባለቤት እና ማኔጂንግ ዳይሬክተር የነበረው ጋዜጠኛ ሚሊዮን ሹሩቤ በስደት በሚገኝበት ናይሮቢ ኬኒያ ዛሬ ጥቅምት 3 ቀን 2007 ዓ.ም. በድንገት ህይወቱ አልፏል፡፡ ኢህአዴግ መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት በጅምላ ያደረገውን የመፅሔቶች እና ጋዜጣ ክስ እና የበርካታ ጋዜጠኞችን እና ብሎገሮችን እስርን ፍርሃት ተከትሎ በቅርቡ ከተሰደዱ ጋዜጠኞች መካከል ጋዜጠኛ ሚሊዮን ሹሩቤ አንዱ ነበር፡፡
ሚልዮን ሹርቤ
ጋዜጠኛው በስደት ኬኒያ ከሚገኝበት አንድ ናይሮቢ ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቢቆይም ህይወቱን ማትረፍ እንዳልተቻለ ታውቋል፡፡ ጋዜጠኛው ከኢትዮጵያ ከተሰደደ ገና ሁለት ወር እንኳ እንዳልሞላው ለማወቅ ተችሏል፡፡ ጋዜጠኛው የድርሰት ስራም እንዳለው ተጠቁሟል፡፡ አዲስ ሚዲያም ለጋዜጠኛ ሚሊዮን ፈጣሪ ነፍሱን በገነት እንዲያኖር፤ ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹና አድናቂዎቹ መፅናናትን ይመኛል፡፡
maraki-magazine
ምንጭ፡ አዲስ ሚድያ

ከወያኔ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሾልኮ የወጣ

mof
ይህ ባለ 16 ገጽ ዘገባና ሰነድ ሲሆን ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ::

Sunday, October 5, 2014

ቅድመ ምርጫ 2007 እና የተቃውሚዎች እጣ ፋንታ (ሀይለሚካሄል ክፍሌ ከኖርዌይ ኦስሎ)

Election2007
ሀይለሚካሄል
መቼም የምርጫ ነገር ሲነሳ በኢትዮጵያ ታሪክ የጎላ ቀለም ያለው ምርጫ 97 ነው ምክንያቱም ከዚ በፊት የነበሩት ምርጫዎች በኢህአዲግም ሆነ በደርግ መንግስት የነበሩት የይስመላ ምርጫዎች ነበሩ ምርጫ 97ም ቢሆን የዲሞክራሲ ጭላንጭል የታየበት በአዲስ አበባ እስከ ምርጫው እለት ሲሆን በክልሎች ግን ምርጫው አንድ ወር እስኪቀረው ነበር በክልሎች ገዝው ኢህአዲግ ቀሪውን አንድ ወር አፈናውን እናወከባውን አጠናክሮ ከመቀጠሉም በላይ አልፎ አልፎ ጠንካራ ተፎካካሪዎች ባሉበት ክልል ግድያም ይፈፅም ነበር በአዲስ አበባም ቢሆን ከምርጫው ውጤት በዃላ የምርጫውን ውጤት በመቀልበስ የዲሞክራሲ ጭላንጭሉን አጨልሞታል ከዚያም በዃላ የምርጫውን ውጤት ተከትሎ በሃይል ገንፍሎ የወጣውን የህዝብ ቁጣ በሃይል ከመቀልበስ ውጭ አማራጭ ያጣው ኢህአዲግ አፈናውን እና ግድያውን አጠናክሮ በመላ ሃገሪቱ ቀጠለ እናም ተቀዋሚ ጎራው እጣ ፋንታውግማሹ እስር ቤት ግማሹም ኢህአዲግ ባሰመረለት መንገድ መሄድ ብቻ ሆነ እናም የምርጫ 97 ድራማ በዚህ መልኩ ተጠናቀቀ ቀሪው አምስት አመት ቀጣዩ ምርጫ እስኪመጣ ግምት ሰጥቶት የነበረውን የምክር ቤቱን ከ540አካባቢ መቀመጫ አንድ አራተኛ ለተቀዋሚ በመስጠት ያለውን የውጭ ጫና በማቅለል የተዘጉትን የእርዳታ ማእቀብ ለማስለቀቅ የሰራው የሂሳብ ስሌት ባለመሳካቱ እራሱን እንዲፈትሽ ምርጫው ትልቅ ማሳያ ሆኖታል በምርጫው ማግስት ኢህአዲግ ውጤቱን በሃይል መቀልበሱ በብዙዎች ቢታመንም ለኢህአዲግ ግን ውጤቱ ያልጠበቀው እና ያልተዘጋጀበት በመሆኑ በቀጣዩ የምርጫ ጊዜ ኢህአዲግ ካለፈው ተምሮ ብዙ ነገሮችን እንደሚያስተካክል የብዙዎች ግምት ቢሆንም ፓርቲው ግን ካለፈው ተምሬአለሁ የሚለውን የምፀት አባባል በአደባባይ እየተናገረ ለቀጣዩ 2002 የምርጫ ዘመን የሚከተለውን መዋቅር ዘረጋ
ከምርጫ 97 በዃላ በዋነኛነት የተወሰዱ እርምጃዎች 1 በህትመት እና በህትመት ውጤቶች ላይ ጫና መፍጠር እና አፋኝ የሆኑ የፕሬስ ህግ አዋጆችን መተግበር
2 በፀረ-ሽብር እንቅስቃሴ ከአሜሪካ ጋር በህብረት ፀረ-ሽብርተኝነትን መከላከል መርህ ሰበብ በምስራቅ አፍሪካ የአሜሪካ ዋነኛ አጋር በመሆን ጠቀም ያለ ወታደራዊ የቁስ እና የገንዘብ ድጋፍ ኢህአዲግ መራሹመንግስት እንደሚያገኝ ይታወቃል መንግስት ይሄንን የሽብር ጥቃት መከላከል በብ በመጠቀም በሃገርውስጥ የፀረ- ሽብር አዋጅ በማቋቋም ብሎም በመተግበር በሃገርውስጥ በሰላማዊ ትግል የተደራጁትን ፓርቲዎችን እና የነፃነት እና ዲሞክራሲ እጦት ተቋውሞ እንቅስቃሴዎችን በሽብርተኝነት በመፈረጅ አዋጁን በመጠቀም ብዙዎችን ለእስር በመዳረግ የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴዎችን መድረክ ማጥበብ ማቀጨጭ እና ብሎም ማጥፋት
3 በምርጫ 97 ከታዩት ጉልህ የኢህአዲግ ስህተቶች ወጣቱን በተለይ ሰራአጥ ወጣቶችን በአደገኛ ቦዘኔነት መፈረጅ እንዲሁም የተማረውን ሃይል ማግለል ስለነበር ይህንን እንደፓርቲው ስህተት በመቁጠር የሙሁሩን ጎራ በከፊልም ቢሆን መተካካት በሚል መርህ ጥቂት ጥቅማጥቅሞችን በማጋራት ብሎም ሙያዊ ሹመቶችን በመስጠት ልማታዊ ሙህር ልማታዊ ጋዜጠኛ ልማታዊ ዶክተር ወ.ዘ.ተ እያለ ወደዱም ጠሉም የፓርቲው አባል ማድረግ
4 ስራ አጥ ወጣቶችን በየቀበሌው እንዲደራጁ በማድረግ ባቋቋማቸው የማታለያ ገንዘብ ብድር ተቋማት ብድር በመፍቀድ እንዲደራጁ በመፍቀድ ሲደረግ ለዚህም የመጀመራያው መስፈርት የድርጅቱ አባል መሆን ሲሆን ለዚህም ዋናው አላማ ለተቀዋሚው ጎራ አባል ለመሆን እየሄደ የለውን ወጣት በጥቅማጥቅም ማስቀረት
5 ቀሪውን የህብረተሰብ ክፍል በተለይ ቀበሊ ነዋሪዎችን አንድ ለአምስት መርህ በኢህአዲግ ቋንቋ(መጠርነፍ)መያዝ እና በህዝቡ ቁጥር ልክ የሚመስል የደህንነት ሃይል ማሰማራት ይሄውም ተቀዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በህዝቡውስጥ ገብተው ምንም አይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ ማድረግ
6 ልማታዊ መንግስት በሚል መርህ በየመንደሩ በእርዳታ ድርጅቶች የተሰሩትን የውስጥ ለውስጥ መንገዶች በኮብል እስቶን በመቀየርለዚሁም በአብዛኛው ሰራ የሌላቸውን ወጣቶችን በማሰማራት አላማው ጥሩ ቢሆንም ከህብረተሰቡ የሚጠየቀው ገንዘብ ግን የተጋነነ ነው::
ኢህአዲግ ግን በዚህ ሲስተም በአንድድንጋይ ሁለት ወፍ የሚለውን የአባቶች አባባል ተጠቅሞበታል ይሄውም በልማት ሰበብ ለአባላቱ ጠቀም ያለ ገንዘብ ማስገኘት እና ሌላው አዳዲስ አባሎችን ማብዛትነው እንግዲህ እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትን የኢህአዲግ የ2002 የምርጫ ዝግጅት ማስቀየሻ ስልቶች ሲሆኑ እንደእቅዱ ሲተገበር ያተረፈው ነገር እጅግ ብዙ ቁጥር ያለው ደጋፊ ማፍራት ቢሆንም እውነታው ግን ኢህአዲግ ያፈራው እውነተኞቹን ደጋፊዎችን ሳይሆን በጥቅም የታሰሩትን እና ለሆዳቸው የተገዙ ደጋፊዎችን ሲሆን የዚህም የመጨረሻ ውጤት የደጋፊው ቁጥር በጨመረ ቁጥር የሁሉንም ጥቅም መጠበቅ አይቻልም ደጋፊዎችም ጥቅመኞች ስለሆኑ ልማታዊ ሳይሆኖ በተቃራኒው ሙሰኞች እና ዘራፊዎች ናቸው እናም የኢህአዲግ ጠላቶች የሚመነጩት ከራሱ ደጋፊዎች ሲሆን እነሱም እነዚህ በጥቅም የመጡቱ ጥቅማቸው በተቋረጠ ጊዜ የኢህአዲግ የመጨረሻ ጠላቶች ናቸው እንግዲህ ከላይ በጠቀስናቸው የማስቀየሻ ስልቶች ኢህአዲግ ምርጫ 2002ን ያለምንም ተቀናቃኝ ምርጫውን 99ፐርሰንት አሸንፌአለሁ ለማለት አስችሎታል ለዚሁም በአሸነፈ ማግስት የቀድሞው ጠ/ሚኒስት ሲናገሩ‹‹ ይህ ህዝብ ኢህአዲግ ካለፈው ስህተቱ የሚማር ፓርቲ መሆኑን ተገንዝቦ ለ5አመት ኮንትራቱን ሰጥቶናል ይህ ለኛ ትልቅ ማስጠንቀቂያ ነው ቃላችንን ካልጠበቅን በድምፁ የሰጠንን ካርድ መልሶ ይነጥቀናል›› ሲሉ አቶ መለስ የንቀት ንግግር አድርገዋል በአንፃሩ ግን እንዴት እንዳሸነፉ እራሳቸውም ህዝቡም ያውቃል እናም የ2002 ምርጫ እንከን የለሽ ምርጫ በሚል ድራማ ተጠናቋል በቀጣዩ መጣጥፍ በምርጫ 2007 ዘገባ ላይ ያተኮረ የዚህን መጣጥፍ ክፍል ሁለት ይዤ እቀርባለው እስከዚያው ቸር ይግጠመን

Monday, September 22, 2014

UN experts urge Ethiopia to stop using anti-terrorism legislation to curb human rights


UN experts urge Ethiopia to stop using anti-terrorism legislation to curb human rights

GENEVA (18 September 2014) – A group of United Nations human rights experts* today urged the Government of Ethiopia to stop misusing anti-terrorism legislation to curb freedoms of expression and association in the country, amid reports that people continue to be detained arbitrarily.

The experts' call comes on the eve of the consideration by Ethiopia of a series of recommendations made earlier this year by members of the Human Rights Council in a process known as the Universal Periodic Review which applies equally to all 193 UN Members States. These recommendations are aimed at improving the protection and promotion of human rights in the country, including in the context of counter-terrorism measures.
“Two years after we first raised the alarm, we are still receiving numerous reports on how the anti-terrorism law is being used to target journalists, bloggers, human rights defenders and opposition politicians in Ethiopia,” the experts said. “Torture and inhuman treatment in detention are gross violations of fundamental human rights.”
“Confronting terrorism is important, but it has to be done in adherence to international human rights to be effective,” the independent experts stressed. “Anti-terrorism provisions need to be clearly defined in Ethiopian criminal law, and they must not be abused.”
The experts have repeatedly highlighted issues such as unfair trials, with defendants often having no access to a lawyer. “The right to a fair trial, the right to freedom of opinion and expression, and the right to freedom of association continue to be violated by the application of the anti-terrorism law,” they warned.

“We call upon the Government of Ethiopia to free all persons detained arbitrarily under the pretext of countering terrorism,” the experts said. “Let journalists, human rights defenders, political opponents and religious leaders carry out their legitimate work without fear of intimidation and incarceration.”
The human rights experts reiterated their call on the Ethiopian authorities to respect individuals’ fundamental rights and to apply anti-terrorism legislation cautiously and in accordance with Ethiopia’s international human rights obligations.
“We also urge the Government of Ethiopia to respond positively to the outstanding request to visit by the Special Rapporteurs on freedom of peaceful assembly and association, on torture and other cruel, inhuman or degrading treatment or punishment and on the situation of human rights defenders,” they concluded.
ENDS
(*) The experts: Special Rapporteur on the promotion and protection of human rights and fundamental freedoms while countering terrorism, Ben Emmerson; Special Rapporteur on the rights to freedom of peaceful assembly and of association, Maina Kiai; Special Rapporteur on the promotion and protection of the right to freedom of opinion and expression, David Kaye; Special Rapporteur on the situation of human rights defenders, Michel Forst; Special Rapporteur on the Independence of Judges and Lawyers, Gabriela Knaul; Special Rapporteur on torture and other cruel, inhuman or degrading treatment or punishment, Juan Méndez.
Special Procedures is the largest body of independent experts in the United Nations Human Rights system. Special Procedures is the general name of the independent fact-finding and monitoring mechanisms of the Human Rights Council that address either specific country situations or thematic issues in all parts of the world. Currently, there are 38 thematic mandates and 14 mandates related to countries and territories, with 73 mandate holders. 

Special Procedures experts work on a voluntary basis; they are not UN staff and do not receive a salary for their work. They are independent from any government or organization and serve in their individual capacity

ohchr

CPJ- ባለፉት ዘጠኝ ወራት አገር ጥለው የተሰደዱት ጋዜጠኞች ቁጥር 34 ደርሷል


cpj-logo-150   CPJ-የተባለው የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ባለፈው ሳምንት በለቀቀው ሪፖርት በአለፉት አስር አመታት ለስደት የሚዳረጉ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ቁጥር ከአለም አንደኛ ነው ብሏል።  የኢትዮጵያዉን ጋዜጠኞች መሰደድ CPJ በሚል ምፃረ-ቃል የሚጠራዉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት እንዳስታወቀዉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ሐገር ጥለዉ የተሰደዱት ኢትዮጵያዉን ጋዜጠኞች ቁጥር ከሠላሳ በልጧል።ሰሞኑንም ሰዎስት ጋጠኞችና አሳታሚዎች ተሰደዋል በተደጋጋሚ ተነግሯል።ዛሬም እንደግመዋል።የኢትዮጵያ መንግሥት የሚደርስባቸዉን ጫና ሽሽት ሐገር ጥለዉ የሚሰደዱት የነፃ ወይም የግል ጋዜጠኞች ቁጥር እያሻቀበ ነዉ።CPJ በሚል ምፃረ-ቃል የሚጠራዉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት እንዳስታወቀዉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ሐገር ጥለዉ የተሰደዱት ኢትዮጵያዉን ጋዜጠኞች ቁጥር ከሠላሳ በልጧል።ሰሞኑንም ሰዎስት ጋጠኞችና አሳታሚዎች ተሰደዋል።በመሆኑም አገር ጥለው የተሰደዱት ጋዜጠኞች ቁጥር 34 ደርሷል፡፡ በአሁኑ ወቅት ገዥው ፓርቲ ከሚወስደው አፈና፣ የማተሚያ ቤትና ሌሎችም ችግሮች ተዳምረው የስደተኛ ጋዜጠኞች ቁጥር ከዚህም እንደሚያሻቅብ ይጠበቃል፡፡ በቅርብ የተሰደዱት ጋዜጠኞች የደህንነት ሁኔታ አንጻር ስማቸውን መጥቀስ አልፈለኩም፡፡ እስካሁን አገር ጥለው የተሰደዱ ጋዜጠኞች ስም ዝርዝር
1.  ጋዜጠኛ በትረ ያቆብ (የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ ፕሬዝደንት፣ የኢቦኒ መጽሄት አምደኛ፣ የአሳማን መጽሄት ኮረስፖንዳንት፣ የዳይሊ ጆርናሊስት ቋሚ ጸሃፊ፣ የኢካድፍ         ፎረም ጸሃፊ፣ የኢትዮጵያ ሆት ክለብ ብሎገር)
2.  ጋዜጠኛ ተሰማ ደሳለኝ (የኢቦኒ መጽሄት ማኔጅንግ ኢዲተር)
3.  ጋዜጠኛ ዘሪሁን ሙሉጌታ (የሰንደቅ ጋዜጣ ከፍተኛ ሪፖርተር፣ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ የህዝብ ግንኙነት)
4.  መላኩ አማረ (የሊያ መጽሄት ማኔጅንግ ኢዲተርና ባለቤት)
5.  ጋዜጠኛ ግዛው ታዬ (የሎሚ መጽሄት ማኔጂንግ ዳይሬክተር)
6.  ጋዜጠኛ ቶማስ አያሌው (የአፍሮ ታይምስ ማኔጅንግ ዳይሬክተር)
7.  ጋዜጠኛ ሰብለወርቅ መከተ (የሎሚ መጽሄት ከፍተኛ ሪፖርተር)
8.   ጋዜጠኛ አቦነሽ አበራ (የሎሚ መጽሄት ከፍተኛ ሪፖርተር)
9.   ጋዜጠኛ ሰናይ አባተ (የሎሚ መጽሄት ዋና አዘጋጅ)
10.  ጋዜጠኛ አስናቀ ልባዊ (የጃኖ መጽሄት ማኔጂንግ ዳይሬክተር)
11.  ጋዜጠኛ ሲሳይ ሳይሌ (የፒያሳ መጽሄት ማኔጂንግ ዳይሬክተርና ባለቤት)
12.  ጋዜጠኛ ሐብታሙ ቦጋለ (የቀድሞ ፍትህ ጋዜጣ ሪፖርተር እና የአንድነት ፓርቲ ሚዲያ ዳይሬክተር)
13.  ጋዜጠኛ እንዳልካቸው ተስፋዬ (የአዲስ ጉዳይ መጽሄት ማኔጂንግ ዳይሬክተርና የሮዝ አሳታሚ ድርጅት ስራ አስኪያጅ)
14. ጋዜጠኛ ኢብራሂም ሻፊ (የአዲስ ጉዳይ መጽሄት ምክልት ዋና አዘጋጅ)
15. ጋዜጠኛ እንዳለ ተሺ (የአዲስ ጉዳይ መጽሄት ከፍተኛ አዘጋጅ)
16. ጋዜጠኛ ሀብታሙ ስዩም (የአዲስ ጉዳይ መጽሄት አምደኛ፣ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ ገንዘብ ያዥ)
17. ጋዜጠኛ ዳዊት ሶሎሞን (የፍኖተ ነጻነት አዘጋጅ፣ የላይፍ መጽሄት ዋና አዘጋጅ፣ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ አመቻች ኮሚቴ አባል)
18. ጋዜጠኛ ዳንኤል ድርሻ (የሎሚ መጽሄት ሚዲያ ዳይሬክተር)
19. ጋዜጠኛ ብስራት ወ/ሚካኤል (በተለያዩ ጋዜጦች፣ መፅሔቶች የራሱ “አዲስሚዲያ” ብሎግን ጨምሮ በተለያዩ ድህረ-ገፆች አዘጋጅ እና ፀሐፊ
20. በቅርቡ የተሰደዱት አስራ አምስት(15) ጋዜጠኞች የደህንነት ሁኔታ አንጻር ስማቸውን መጥቀስ አልፈለኩም፡፡ እነዚህ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች የጋዜጠኛ ሞያ ስነምግባሩን በመጠቀም የተለያዩ የፖለቲካ፣ ሰብዓዊ መብት ጥሰትና ማኀበራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገው በራሳቸውና በተለያየ የብዕር ስሞች እንደሚፅፉ ይታወቃል፡፡ ጋዜጠኞቹ ከዚህ በፊትም በመንግስት ደህንነት ኃይሎች በተለያየ ስፍራዎች እገታ አልፎ ተርፎም ዕስር ድብደባና እንዲውም (በተመሳሳይ ፆታ) ኢፆታዊ ጥቃት፣ ከስልክ ጠለፋ እስከ ዛቻና ማስፈራራት ይደርስባቸው እንደነበር ከዚህ ቀደም የወጡ መረጃዎች ቢያመለክቱም፤በተለይ ከጥቅምት 2006  ዓ.ም. ከአዲሱ ጋዜጠኞች ማኀበር መመስረት ሂደት ጀምሮ እና በሚያዚያ ወር 2006 ዓ.ም. 3 ጋዜጠኞችን እና 6 የዞን 9  ብሎገሮች በመንግስት ከታሰሩ በኋላ የመንግስት ደህንነቶች ክትትል ከበፊቱ በበለጠ ሁኔታ ተጠናክሮ መቀጠሉንና ቀጣዩ እስረኞች እነሱ እንደሚ ሆኑ በግልፅ ይነገራቸው ነበር በቅርቡ ከታሰሩት ጋዜጠኞችና ብሎገሮች የእስር ስም ዝርዝር ውስጥ ስማቸው በግንባር
ቀደምነት እንደሰፈረና በዕነርሱም ዙሪያ መረጃ እየሰበሰበ መሆኑ ምንጮች አረጋግጠው እንደነበረ ይታወቃል፡፡ ቀደም ሲል የማኀበሩ ፕሬዘዳንት ጋዜጠኛ በትረ ያዕቆብ፣ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ጋዜጠኛ ዘሪሁን ሙሉጌታ፣የህዝብ ግንኙነት ምክትል ኃላፊው ጋዜጠኛ ሐብታሙ ቦጋለ እንዲሁም የአንድነት ገንዘብ ያዥ ማይክል ጌታሁን እና መስራች አባል ጋዜጠኛ ተሰማ ደሳለኝ መሰደዳቸው አይዘነጋም፡፡ በአጠቃላይ ጋዜጠኛ ብስራት ወ/ሚካኤልን ጨምሮ በ2006 ዓ.ም. ብቻ 34 የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ሲሰደዱ፤3 የውጭ ዜጎች ጋዜጠኞችን ጨምሮ 20 ጋዜጠኞችና ብሎገሮች ደግሞ በእስር ላይ እንደሚገኙ ታውቋል፡፡ በኢትዮጵያ ፍትሕ ሚኒስቴር መከሰሳቸውን ተከትሎ ሀገር ጥለው የተሰደዱ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች የደኅንነት ስጋት ገጥሞናል ይላሉ። የጋዜጠኞቹ የደኅንነት ስጋት ተዓማኒ ከሆነ ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት የኬንያ ፅ/ቤት ተናግሯል። አቶ ግዛው ታዬ የሎሚ መጽሔት ስራ አስኪያጅ ነበሩ። በመጽሔታቸው በወጡ ጽሁፎች ድርጅቱና ሥራ አስኪያጆቹ ሐሰተኛ ወሬ አትሞ በማውጣትና ሕዝብን በማነሳሳት ወንጀል’ በሚሉ ሁለት ክሶች ሰኔ 6 ቀን 2006 ዓ.ም በኢትዮጵያ ፍትሕ ሚኒስቴር መከሰሳቸውን ተከትሎ ፍርድ ቤት ቆመውም ነበር። አቶ ግዛው ታዬ በመጀመሪያው የፍርድ ቤት ውሎ የተጠየቁትን የ50 ሺህ ብር ዋስትና አስይዘው ሌላ ቀጠሮ ከተቀበሉ በኋላ ግን በኢትዮጵያ አልቆዩም። እርሳቸው የኢትዮጵያ መንግስት ያስረኛል ወይም ሌላ ጠንካራ እርምጃ ይወስድብኛል በሚል ስጋት ከሃገር ለመውጣት ቢችሉም አሁን ባሉበት ሃገር የደህንነት ስጋት ተሰምቶኛል ይላሉ። የአፍሮ ታይምስ ጋዜጣ ስራ አስኪያጅ አቶ ቶማስ አያሌው ና የጃኖ መጽሄት ስራ አስኪያጅ አቶ አስናቀ ልባዊም ከኢትዮጵያ ከተሰደዱ ጋዜጠኞች መካከል ይገኙበታል።አቶ ግዛው ታዬ እንዲሁም ጋዜጠኛ ሐብታሙ ቦጋለን ጨምሮ አሁን በጎረቤት ሃገር በአብሮነት የሚኖሩት ሶስቱ የግል-ፕሬስ ባለሙያዎች የደህንነት ስጋት ተደቅኖብናል ይላሉ። የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት የኬንያ ቢሮ ቃል አቀባይ ኢማኑኤል ኒያቤራ የደህንነት ስጋትን ጨምሮ በተለያዩ ምክንያቶች ከ14 የተለያዩ ሃገራት የመጡ ስደተኞች መኖራቸውንና ይናገራሉ። የሶስቱን ጋዜጠኞች የደህንነት ጉዳይ ተጠይቀው ሃሳብ ከመስጠት የተቆጠቡት ቃል አቀባዩ የተለያዩ ድጋፎች እንደሚያደርጉ ግን ተናግረዋል። ”የመጡት በተለያዩ ፈተናዎች ምክንያት ነው። ይህ የደህንነት ስጋትን ይጨምራል።ለምሳሌ የኢትዮጵያውያኑ ጉዳይ ተዓማኒ መሆኑን ለማረጋገጥ ቃለ-መጠይቅ እናደርግላቸዋለን። ጉዳያቸው ተዓማኒ ሆኖ ስናገኘው ደህነታቸው ሊጠበቅ የሚችልበትን እርምጃ እንወስዳለን። ለፖሊስ ጣቢያዎች በቀረቡና ደህንነታቸው የተጠበቀ አካባቢዎች እናስቀምጣቸዋለን። ልዩ ትኩረት እንዲያገኙም እናደርነጋለን። ለምሳሌ አንዳንዶቹ ያለባቸው የደህንነት ስጋት በቋሚነት እስኪቀረፍ ድረስ ወደ አደባባይ መውጣት ስለማይችሉ የሚፈልጉትን አግልግሎት እና ምግብ እናቀርባለን።” በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት ድረ-ገጽ መረጃ መሰረት 19,920 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በኬንያ የሚገኙ ሲሆን 11,670ው ጥገኝነት ፈላጊዎች ናቸው እንዲሁም በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት ድረ-ገጽ መረጃ መሰረት 16,200 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በግብፅ ካይሮ የሚገኙ ሲሆን 16,200ው ጥገኝነት ፈላጊዎች ናቸው ፍርድ ቤት የተሰደዱ ጋዜጠኞችን ጉዳይ በሌሉበት ማየቱን ቀጥሏል
ጳጉሜን ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት በመግለጫ የከሰሳቸው ጋዜጠኞች አግር ጥለው ከወጡ በሁዋላ ጉዳያቸው በሌሉበት እየታየ ነው። ከሳምንት በፊት ጥሪ ተደርጎላቸው እንዲቀርቡ የታዘዙት የፋክት፣ አዲስ ጉዳይ እና ሎሚ መጽሄት አዘጋጆችና ባለቤቶች ፍርድ ቤት ለመቅረብ ባለመቻላቸው 17ኛው ወንጀል ችሎት ጉዳያቸውን በሌሉበት ለማየት ተጨማሪ ቀጠሮ ሰጥቷል። ተከሳሾቹ የመንግስታዊ ስርዓቱን በአመጽ ለማፍረስ አስበዋል የሚል ክስ የተመሰረተባቸው ሲሆን፣ እንደማስረጃም የቀረበው ህዝቡን ለአመጽ የሚያነሳሱ ጽሁፎችን አትመው አሰራጭተዋል የሚል ነው። የሎሚ መፅሄት ስራ አስኪያጅ አቶ ግዛው ታዬ ቀድም ብሎ ፍርድ ቤት በቀረሩበት ወቅት በ50 ሺ ብር ቢለቀቁም ከዚያ በሁዋላ በነበሩት ችሎቶች ባለመገኘታቸው ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ እንዲሆን ፍርድ ቤት ወስኗል። ባለፉት ጥቂት ቀናት የወጡትን የማራኪ መጽሄት ባለቤትና አዘጋጅ ሚሊዮን፣ የቃል ኪዳን መጽሄት አዘጋጅ ኤለያስ ጉዲሳ እና የአዲስ ጉዳይ ዘጋቢ መድሃኒት ረዳን ጨምሮ የተሰደዱት ጋዜጠኞች ቁጥር 34 ደርሷል። ኢትዮጵያ በሚሰደዱ ጋዜጠኞች ቁጥር በአለም ላይ የመጀመሪያውን ደረጃ ይዛ ትገኛለች ዘረኛውና አምባገነናዊው የወያኔ አገዛዝ ባለፉት አስር አመታት ለስደት የዳረጋቸው ጋዜጠኞች ቁጥር ከአለም አንደኛው ነው ተባለ June 25, 2010 | Filed underዜና | Posted by admin ሲ.ፒ.ጄ. የተባለው የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ባለፈው ሐሙስ በለቀቀው ሪፖርት በአለፉት አስር አመታት ለስደት የሚዳረጉ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ቁጥር ከአለም አንደኛ ነው ብሏል። በነዚህ አስር አመታት ስልሳ ሁለት ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች አገራቸውን ጥለው የተሰደዱ ሲሆን፤ ይህም እስርን፣ ጥቃትን እና ማስፈራራትን ሽሽት እንደሆነ ታውቋል። ባለፈው አመት ብቻ አስራ አምስት ጋዜጠኞች ከኢትዮጵያ እንደሸሹ እና ይህም ነፃው ፕሬስ ያለበት ሁኔታ እየከፋ ስለመሄዱ ማስረጃ ነው ሲል ሪፖርቱ ገልጿል። የወያኔ አገዛዝ የግል መገናኛ ብዙሃንን ነፃነት የሚገድብ ህግ ከማውጣት አንስቶ ጋዜጠኞችን እንዳሻው በማሰር፤ በመክሰስ እና በማስፈራራት ከሞላ ጎደል ነፃውን ፕሬስ መዝጋቱ ይታወቃል። ከኢትዮጵያ ውጭ የሚገኙ ገለልተኛ እና ተቃዋሚ መገናኛ ብዙሃንም ለኢትዮጵያውያን እንዳይተላለፉ ከፍተኛ የአፈና ዘመቻ ያካሂዳል። በተያያዘ ዜና አገዛዙ ሄዘር መርዶክ የተባለችን የአሜሪካ ድምጽ ዘጋቢ ከአገር ማስወጣቱ ታውቋል።
የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር ወይም ኦብነግ የወያኔ ጦር በኦጋዴን 71 ንጹሃን ዜጎችን ገድሏል በሚል በመግለጫው ያወጣውን ክስ ለመመርመር ምስራቅ ኢትዮጵያ የተጓዘችው ሄዘር መርዶክ ባቢሌ ከተማ አካባቢ ለሁለት ቀናት መታሰሯን ብሉምበርግ የዜና አውታር ዘግቧል። ስለጉዳዩ የተጠየቀው በረከት ስምኦን ጋዜጠኛዋ “የኦብነግን ሰዎች ስትፈልግ” ነበር ያለ ሲሆን፤ እሷም በበኩሏ “ኢትዮጵያ ውስጥ ሰዎችን ማናገር ወንጀል መሆኑን አላውቅም ነበር” ብላለች። ጋዜጠኛዋ ሐሙስ እለት ከኢትዮጵያ እንድትወጣ መደረጉ ታውቋል።
ባለፈው የፈረንጆች አመት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ አገራት የፖለቲካ ጥገኝነት መጠየቃቸው ታወቀ እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር በ2009 አመተ ምህረት 42500 ኢትዮጵያውያን በተለያዩ አገራት የፖለቲካ ጥገኝነት መጠየቃቸውን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን በሰጠው መግለጫ አስታወቀ። ይህ ቁጥር በእርስ በርስ ጦርነት የምትታመሰውን ሶማሊያ በዛው አመት ከሸሹት ሰዎች ቁጥር በአራት ሺህ ስድስት መቶ እንደሚበልጥ ታውቋል። ከነዚህ ኢትዮጵያውያን ውስጥ 84 በመቶ የሚሆኑት ወደ ሶማሊያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ግብፅ እና ኬንያ ሄደዋል። ይህ ቁጥር የተሰበሰበው ስደተኞቹ ለየሄዱባቸው አገራት መንግስታት እና ለስደተኛ ድርጅቱ የፖለቲካ ጥገኝነት ለማግኘት ባቀረቧቸው ማመልከቻዎች አማካኝነት ስለሆነ የአጠቃላይ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ቁጥር አይወክልም። በያመቱ አገራቸውን ጥለው የሚሰደዱ ቁጥራቸው የማይታወቅ ኢትዮጵያውያን የፖለቲካ ጥገኝነት እናገኛለን ብለው ስለማይገምቱ በተለያዩ ሃገራት በህገወጥነት እንደሚኖሩ ይታወቃል። በተጨማሪም፥ ቁጥሩ የጉልበት ስራ ፍለጋ ወደ መካከለኛው ምስራቅ እና ሌሎች አገራት በህጋዊ መንገድ የሚሄዱትን የኢኮኖሚ ስደተኞች አያካትትም። የወያኔ አገዛዝ በኢትዮጵያ ያለው የኢኮኖሚ ሁኔታ እየተሻሻለ እና አገሪቱ ወደ ዴሞክራሲ እየሄደች መሆኑን ደጋግሞ ቢናገርም፤ በአስርት ሺሆች የሚቆጠሩ ዜጎች በየአመቱ አገራቸውን እየጣሉ መሰደዳቸው አገዛዙ የሚለው ተቃራኒ እውነት ለመሆኑ ምስክር ነው ሲሉ የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ።